፤ የደቡቡ የአሜሪካ ክፍል የባርነት ሥርዓትን የሚደግፍ፣ የሰሜኑ የአሜሪካ ክፍል የባርነት ሥርዓትን የሚቃወም ነበር፤ ሊንከልን ሁለቱን ወገኖች ለማስማማት ሞከረ፤ ጦርነትን አልፈለገም፤ ግን አገሩም አንዲገነጠል አልፈለገም፤ መሠረቱ የተከፋፈለ ቤት አይቆምም፤ ስለዚህም ጦርነትን አልፈራም፤ ዛሬ በዓለም ሁሉ ገናና፣ ኃይለኛና ሀብታም አገርን ፈጠረ፡፡ ከሀጫሎ ሞት አስቀድሞ የሚታገዱ አፍራሽ ኃይሎች መረን ባይለቀቁ ሀጫሎም አይሞትም፤ የተከተለው ጥፋት ሁሉ ምንልባትም አይፈጸምም ነበር፤ የወያኔን ሹማምንት በጊዜ ዳር ማስያዝ ቢቻል ኖሮ የዛረው ራስ ምታት አይደልቀንም ነበር፡፡አውቃለሁ በቢሆን-ኖሮ አስተሳሰብ ታሪክ አይጻፍም! ከስሕተት ለመማር ግን ይረዳል፡፡
መስፍን ወልደ ማርያም መስከረም 2013
Source: Link to the Post