መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ባለፈው አመት ካመረተው የስሚንቶ ምርት አብዛኛውን ለምሽግ ስራ መዋሉ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸ…

መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ባለፈው አመት ካመረተው የስሚንቶ ምርት አብዛኛውን ለምሽግ ስራ መዋሉ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ድርጅቱ በመቀሌ በሚገኘው ፋብሪካው ቀደም ባሉት ግዜያት ከምርቱ አብዛኛውን ለመሀል ሀገር ገበያ እንደሚያቀርብ ይታወቃል። ከዛም በለፈ ለህዳሴ ግድብ የምርት ግብአት ከሚያደርጉ የስሚንቶ ፋብሪካዎችም አንዱ ነበር። ሆኖም የኢትዮ ንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ መረጃ እንደሚያሳየው በ2012 የምርት አመት የድርጅቱ ምርት ወደ መሀል ሀገር ለገበያ ከመቅረብ ይልቅ በትግራይ ክልል ሙሉ ለመሉ በሚባል ደረጃ ጥቅም ላይ ሲውል እንደነበር ተገልፆአል። ለዚህም በሲሚንቶ ፋብሪካው ኃላፊዎች በምክንያትነት የቀረበው በከፍተኛ ሁኔታ ትግራይ ውስጥ የግንባታ መስፋፋት እንደሆነ መገመት ነበር። ይሁንና የፋብሪካው ምርት በዋናነት ጁንታው/ ህወሃት ላቀደው ጦርነት የመከላከያ ምሽግ ግንባታ ግብአትነት ሲውል እንደነበር የኬሚካል እና ኮንስትራክሽን ግብአት ኢንደስትሪ ልማት ኢንስትቲዮት ዋ/ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ሀላላ ለኢትዮ የንግድና ኢንሸስትመንት መድረክ ተናግረዋል። ምንጭ: ShegerTimesmagazine

Source: Link to the Post

Leave a Reply