
የትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀለን ጨምሮ በተለያዩ ትግራይ አካባቢዎች የተደራጁ የዘረፋ ድርጊቶች እየተፈጸሙ መሆናቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት ገለጸ። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ቅዳሜ ታኅሣሥ 08/2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የፌደራሉ መንግሥት ሠራዊት ባልደረሰባቸው የትግራይ አካባቢዎች ዘረፋዎች እየተፈጸሙ መሆናቸውን አመልክቷል። ለሁለት ዓመት የተካሄደው ጦርነት በመንግሥት እና በህወሓት መካከል በተደረሰ ስምምነት ከቆመ ከአንድ ወር በላይ ሆኖታል።
Source: Link to the Post