በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ከአንድ ዓመት በላይ በዘለቀ ተከታታይ ጥቃት የበርካታ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ደግሞ ለጉዳት መዳረጋቸ በተለያዩ ጊዜያት ተዘግቧል። በዚህም ሳቢያ የሚፈጠረውን የጸጥታ ችግር ለመቅረፍ የመከላከያ ሠራዊትና የፌደራል ፖሊስን ያካተተ ኮማንድ ፖስት ከተቋቋመ ወራት ተቆጥረዋል። ነገር ግን በአካባቢው ባሉ ነዋሪዎች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት አሁንም እንደቀጠለ ነው።
Source: Link to the Post