“መተሳሰብ እንደ ቤተሰብ ፣ለሀገር እና ለማህበረሰብ” በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የቤተሰብ ቀን እየተከበረ ይገኛል።በአለም አቀፍ ደረጃ ለ30ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ ሁለተኛ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/ei3ofCUlaWu_d3fRBFZb73mD2O7GDM4bWhyb2RnP3hM8ZsoPJwbEHwJ7SbzYeVLjS-nGb0Y5LkdBZldCPx-qyz1ngKDEVxVfvodHkByyVDcmgA5elewTME7jltJcRBCL3KtBzVGpDzUGcmZGVcBGbYzViJS6gP6r8WClNl85BmTljeC6tkaqJbm5XqgED13mekqkp6dTjnMcjgyhky5DBMpjV-PDVoXAZcNSUUFlARQbXRc_63TgERT2maLkuJZkdDZt4BfaIWQR9ZUjI0qOVr5jSu2yCpTXq9l3_sjhscjZtrO4Hdol9AizB9pog6bBTyJ6lH1tNtCkyNATMUhXAA.jpg

“መተሳሰብ እንደ ቤተሰብ ፣ለሀገር እና ለማህበረሰብ” በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የቤተሰብ ቀን እየተከበረ ይገኛል።

በአለም አቀፍ ደረጃ ለ30ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ ሁለተኛ ጊዜ “መተሳሰብ እንደ ቤተሰብ ፣ለሀገርና ለማህበረሰብ” በሚል መሪ ቃል በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስተር አዘጋጅነት በአዲስ አበባ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።

የዘንድሮ መሪ ቃል የመተሳሰብ ፣የመረዳዳት ፣የመቀራረብ ፣በጋራ ጉዳይ ላይ የመግባባት ፣በቅንጅት የመስራት እሳቤዎችን የሚቀሰቅስ ሀሳብ መያዙ ተመላክቷል።

ቀኑ ሲከበርም የቤተሰብ ሁለገብ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅኦ ለማሳደግ ፣እውቅና ለመስጠት እና ሁሉም ቤተሰብ ለቤተሰብ አባላት ምስጋና እና ክብር የሚሰጥበትን እድል ለመፍጠር አላማውን ያደረገ መሆኑ ተነስቷል።

ቤተሰብ ትውልድን የመተካት ፣የልጆችን ስብዕና የመቅረፅ ፣የሀገር ኢኮኖሚን የማሳደግ ፣ለቤተሰብ አባላት ዋስትና የመሆን ትልቅ ሚና ስላለው ቤተሰብ ደህንነቱ ሊጠበቅ እና ተገቢውን ክብር እና ጥበቃ ሊያገኝ እንደሚገባም ተገልጿል።

በሐመረ ፍሬው

ግንቦት 07 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply