You are currently viewing መተከል ማንዱራ ወረዳ ልዩ ቦታው እሪ በከንቱ በሚባል ስፍራ ዛሬ ከ25 በላይ ንፁሀን ተጨፍጭፈዋል! በምን አልባት ይታዬው_ Minalbat Yitayew  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ነሀሴ…

መተከል ማንዱራ ወረዳ ልዩ ቦታው እሪ በከንቱ በሚባል ስፍራ ዛሬ ከ25 በላይ ንፁሀን ተጨፍጭፈዋል! በምን አልባት ይታዬው_ Minalbat Yitayew አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሀሴ…

መተከል ማንዱራ ወረዳ ልዩ ቦታው እሪ በከንቱ በሚባል ስፍራ ዛሬ ከ25 በላይ ንፁሀን ተጨፍጭፈዋል! በምን አልባት ይታዬው_ Minalbat Yitayew አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሀሴ 4 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል በመንደሮች እና በተለያዩ ቦታዋች ውስጥ ተመላልሻለሁ ፡፡ በየቦታው “መንግስት የለም ፡፡ እየሞትን ነው ” ይህ ጩኸት ከእያንዳንዱ የመተከል ክፍል ፣ ከወንበራ ፣ ከድባጤ፣ ከቡለን፣ ከማንዱራ ከጉባ ከፓዌና ከዳንጉር የንፁሀን ድምፅ ይሰማል፡፡ በመተከል ምድር ውስጥ ብዙ ቦታ ረገጥኩ ከሞት በስተቀር ብስራት የለም። ተፈናቃዮች ብዙዎች ቀድሞውኑ በረሃብ እንደሞቱ አውቃለሁ። ተስፋ የቆረጡ ፍትህን በጣም ‘የተራቡ’ ሰዋች እልፍ ናቸው። ሰሚ ስለጠፋ አሁን በየራሳቸው መንገድ መጓዝን መርጠዋል። “ሞትን እየጠበቅን ነው” የከተማ ነዋሪዋች የዘወትር የአቀባበል ንግግር ነው። በከተማዋች በርሀብ ምክንያት ብዙ ቤቶች ቀድሞውኑ ከሞቱ ሰዎች ባዶ ናቸው። በእርግጥ አገር እንደካስማ በተወጠረችበት በዚህ ወቅት ተደራጅቶ አካባቢንና ራስን ከመጠበቅ ውጭ መፍትሄ የለም። ዛሬ ማንዱራ ወረዳ ጅግዳ ቀበሌ ልዩ ስሟ እሪ በከንቱ በሚባል ቦታ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ የመራው አቶ ወረዳ ማካ ይባላል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አፈ ጉባኤ የሆነችው የወ/ሮ አለምነሽ ይባስ ቤተሰብ ነው። የማንዱራውን ጨፍጫፊ ቡድን በመምራት ላይ ያለ ነው። በግልገል በለስ መምህራን ኮሌጅ የተሀድሶ ስልጠና ወስዷል። በእሱ የሚመራው የጉሙዝ ሽፍታ ማንዱራ ወረዳ ብቻ ሶስት ካምፕ ሰርቷል። ጅግዳ ዳቡህ እና ጉማዴ። ከነዚህ ቀበሌዋች እየተወረወረ ይጨፈጭፍል። እነዚህ ቀበሌዋች ለአማራ ክልል እጅግ ቅርብ ናቸው። ነዋሪዋች በእግር የሚወጡና የሚገቡበት ነው። በግልገል በለስ መምህራን ኮሌጅ የተሀድሶ ስልጠና የተሰጠው በወረዳ ማካ የሚመራው የጉሙዝ አማፂ ቡድን ዛሬ በጅግዳ ቀበሌ ልዩ ቦታዋ እሪ በከንቱ በምትባል ስፍራ ሁለት የተሳቢ ሹፌሮችንና ሁለት የህዝብ ማመላለሻ መኪኖችን ከነ ተሳፋሪዋች በማንዱራ ወረዳ ጅግዳ ቀበሌ ልዩ ቦታው እሪ በከንቱ በሚባል ስፍራ ከ25 በላይ ንፁሀን ጨፍጭፏል። በአሁኑ ሰዓት የተሳፋሪ ሰዎችን ስልክ የሚያነሱት ሽፍቶች ናቸው። በሌላ በኩል የከማሽ ዞን በአማፂ ቡድኑ በቁጥጥር ስር ከዋለች ሰነባብቷል። የከማሽ ዞን አስተዳደር እና ፀጥታ ትናንት በአማፂው ተገድሏል። … የሚገርመውና የሚደንቀው ነገር ከቻግኒ ግልገል በለስ ለሚመላለሱ የህዝብ መኪኖችም ሆነ ወደ አባይ ለሚሄዱ መኪኖች እጀባ የሚሰጡት የጉሙዝ ሽፍቶች ናቸው። ጫካ ላይ ሲያርዱ የነበሩ ነብሰ በላዋች እጀባ እንዲያደርጉ የፈቀደው ኮማንድ ፖስቱ ነው። የግልም ሆነ የቡድን መሳሪያ እንዲሁም ሙሉ ተሽከርካሪ የሰጣቸው ኮማንድ ፖስቱ ነው። እልፍ አዕላፍ ነብሶችን ለበላ ቡድን ይህን ያክል እንክብካቤ ሲደረግላቸው ያዩ ታዳጊ የጉሙዝ ወጣቶች የተገነዘቡትና የተማሩት ቀይ በመግደል ክብርና ስልጣን እንደሚገኝ ነው። የመተከል ጉዳይ ረጅምና አጭር እጆች የተቀላቀሉበት በመሆኑ መፍትሄው እንዲሁ ቀላል አይሆንም። ኮማንድ ፖስቱ ዘላቂ መፍትሄ ይዞ አልመጣም። ከሌላ አካባቢ መጥቶ ነፃ ያወጣኛል ብሎ መጠበቅ እና ሰሚ መንግስት አገኛለሁ ብሎ ማሰብ የድንቁርናዎች ሁሉ አናት ነው። መፍትሄው ያለው ከማህበረሰቡ ነው። ተደራጅ ራስህን ተከላከል መንግስት የሚባለው አካል እንደ ግድግዳ ስዕል ሆኗል እንኳን ሊንቀሳቀስ ሊናገር አልቻለም ስትባል ከተሽኮረመምክ የሬሳ ሳጥን አዘጋጅተህ መጠበቅ መብትህ ነው! -መደራጀት -መረጃ መለዋወጥ -ሆድ አደሮችን ማስወገድ ይህ አልቻል ካለ ከሙሉ አቅርቦት ጋር’ ዱር ቤቴ ‘ብሎ መቀመጥ ጊዜውን የዋጀ መፍትሔ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply