መተከል እየተፈጸመ ላለው ተከታታይ ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት የፌደራል መንግስት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ የመተከል ነዋሪዎች ጠየቁ                     አሻራ ሚዲያ…

መተከል እየተፈጸመ ላለው ተከታታይ ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት የፌደራል መንግስት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ የመተከል ነዋሪዎች ጠየቁ አሻራ ሚዲያ…

መተከል እየተፈጸመ ላለው ተከታታይ ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት የፌደራል መንግስት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ የመተከል ነዋሪዎች ጠየቁ አሻራ ሚዲያ ህዳር 26/2013 ዓ.ም ባህር ዳር በመተከል ትናንት ህዳር 25 እና ዛሬ ህዳር 26 ቀን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ያሰማራቸው ታጣቂዎች ከመከላከያ ጋር ውጊያ መግጠማቸውንና ንጹሀንን ሲገድሉ ከታጣቂዎችም በመከላከያ የተገደሉ ስለመኖራቸው የዳንጉር ወረዳ ቆጣ ቀበሌ ነዋሪ የሖኑ ግለሰብ በስልክ ገልጸውልናል፡፡ በእድሜ የገፋሁ ሽማግሌ ነኝ የሚሉት ይህ ግለሰብ ለአሻራ ሚዲያ በስልክ እንደገለጹልን አካባያችን በታጣቂዎች እየታመሰ፤ ንጹሀን በማንነታቸው ብቻ እየተነጠሉ እየተገደሉ፤ እየተፈናቀሉ እና ቤት ንብረታቸው እየተዘረፈ ሶስት ዓመታትን አስቆጠርን ያሉ ሲሆን… የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የጥቃቱ ተባባሪ በመሆኑ ተጠያቂ ሊሆን እንደሚገባው ገልጸውልናል፡፡ እንደ ግለሰቡ ገለጻ ባለፈው ሳምንት ብቻ በዳንጉር ወረዳ ቆጣ በተባለ እሳቸው በሚኖሩበት ቀበሌ ብቻ አስራ አራት የሚሆኑት እንደተገደሉ እና አስክሪናቸው እስካሁን ድረስ ባለመነሳቱ ክፉኛ እንዳሳመማቸው ገልጸውልናል፡፡ በጥቃት አድራሽ ሀይሎች የተነሳ የዘራነው የሰሊጥ፤ የቦቆሎ እና የአኩሪ አተር ሰብል ሳይሰበሰብ በሜዳ ቀርቶብናል የሚሉት ግለሰቡ ለዕለት ደራሽ የሚሆን ምግብ በማጣታችን ለችግር የተዳረግን ሲሆን ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንገኛለን ሲሉም አሁን ላይ ያሉበትን ሁኔታ አብራርተዋል፡፡ በመሆኑም አካባቢውን ከጥፋተኞች ነጻ ለማድረግ እንደከዚህ ቀደሙ በዋዛ ፈዛዛ የሚታይ ጉዳይ ሳይሆን የፌደራል መንግስት በአፋጣን እጁን አስገብቶ እርምጃ እንዲወስድ ፤ እንዲሁም የተገደሉት እንዲቀበሩ እና አጽማቸው በክብር እንደየሀይማኖታው እንዲያርፍ ፤ ለተፈናቃዮች የመቋቋሚያ እና መሰል አስፈላጊ ነገሮች እንዲሟሉ ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡ ዘጋቢ፡¬ ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply