መተከል ድባጤ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች ላይ ተኩስ እንዳለ አሻራ በምሽቱ ሰምቷል፡፡ (አሻራ ጥር 9፣ 2013 ዓ.ም) ለሁለት ዓመታት በተለየ ሁኔታ የቀጠለው የመተከል የንፁሃን ጭፍጨፋ  ዛሬም…

መተከል ድባጤ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች ላይ ተኩስ እንዳለ አሻራ በምሽቱ ሰምቷል፡፡ (አሻራ ጥር 9፣ 2013 ዓ.ም) ለሁለት ዓመታት በተለየ ሁኔታ የቀጠለው የመተከል የንፁሃን ጭፍጨፋ ዛሬም…

መተከል ድባጤ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች ላይ ተኩስ እንዳለ አሻራ በምሽቱ ሰምቷል፡፡ (አሻራ ጥር 9፣ 2013 ዓ.ም) ለሁለት ዓመታት በተለየ ሁኔታ የቀጠለው የመተከል የንፁሃን ጭፍጨፋ ዛሬም በድባጤ ቀጥሏል፡፡በታጣቂው ቡድን በመከላከያ ሳይቀር ጥቃት የተከፈተበት ሲሆን፣ ምን ያህል ሰዎች ተጎዱ የሚለውን አሻራ በትክክል ማረጋገጥ አልቻለም፡፡ በመተከል ያለው ሁኔታ እያደር እየተባባሰ የሄደ ሲሆን፣ የኦነግ ሀይል የቁጥጥር አድማሱን እያሰፋ ንፁሃንን እየጨፈጨፈ ነው፡፡ እስካሁን በወር ውስጥ ብቻ 600 አካባቢ ንፁሃን ታርደው በጫካ የተቀበሩ ሲሆን፣ የንፁሃንን ግድያ በተመለከተ የአማራ ክልል አመራሮች ፀጥ ብለዋል፡፡ ስለመተከል ድምፅ የሚያሰሙ ወጣቶችን በመራዊ ከተማ ዛሬ የከለከሉ ሲሆን፣ ለማሰርም ተንቀሳቅሰዋል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ በጃዊ፣ በዚገም እና በጓንጓ ተከታታይ የጥቃት ሙከራ የኦነግ ሀይል ሲያደርግ ክልሉ ያለው ነገር የለም፡፡ ስለመተከል ትፅፋላችሁ፣ ታስተባብራላችሁ የተባሉት ሁሉ በብዛት በአማራ ብልፅግና በኩል በበጎ እንደማይታዮ ብዙዎች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል የተደረገውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ እና የጫካ ቀብር በተመለከተ አሻራ ሚዲያ በቪዲዮ አቀናብሮ ለሰባዊ መብት ተቋማት እና ለአጋር ሚዲያዎች ይፋ የሚያደርግ ይሆናል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply