መተከል ጥቃቱ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡ (አሻራ ጥር 2፣ 2013 ዓ.ም) በቡለን እና በዳንጉር ባሉ ቀበሌዎች ታጣቂዎች ንፅሃን እያጠቁ ነው፡፡ ቤት እና ንብረት እያቃጠሉ ነው፡፡…  በድባጤ ወ…

መተከል ጥቃቱ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡ (አሻራ ጥር 2፣ 2013 ዓ.ም) በቡለን እና በዳንጉር ባሉ ቀበሌዎች ታጣቂዎች ንፅሃን እያጠቁ ነው፡፡ ቤት እና ንብረት እያቃጠሉ ነው፡፡… በድባጤ ወ…

መተከል ጥቃቱ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡ (አሻራ ጥር 2፣ 2013 ዓ.ም) በቡለን እና በዳንጉር ባሉ ቀበሌዎች ታጣቂዎች ንፅሃን እያጠቁ ነው፡፡ ቤት እና ንብረት እያቃጠሉ ነው፡፡… በድባጤ ወረዳ በሁለት መከላከያዎች ላይ በታጣቂዎች ላይ ጉዳት ሲደርስ፣ አንድ የመከላከያ ሀይል በጉዳቱ ተገሏል፡፡ ጥቃት የደረሰባቸው ንፅሃንም አሉ፡፡ በድባጤ እና በዳንጉር ተጨማሪ ሀይል የገባ ቢሆንም፣ በመተከል መንግስታዊ መዋቅሩ ሙሉ በሙሉ ስለፈረሰ መተከልን ወደ ሰላም መመለስ አልተቻለም፡፡ የመከላከያው ሀይል የታጣቂውን ሁኔታ እና ለመልካአምድሩ አዲስ መሆኑንም ለመተከል ጥቃት ምክንያት ሆኗል፡፡ መተከልን እንዳይረጋጋ የሚፈልግ የውስጥ የብልፅግና ክንፍ፣ በውጭ በግብፅ ተልከው የሱዳን የብሉናይል ግዛት አመራሮች ከታጣቂው ጎን ተሰልፈዋል፡፡ ውስብስቡን የመተከል ጅምላ ጭፍጨፋ ለማስቆም፣ አካታች እና ፍትሃዊ የመንግሥት ግንባታ ያስፈልጋል፡፡ የህግ ማስከበር ሂደቱም በተጨማሪ ሀይል ካልተቀናጀ አደጋው ቀጣይነት ይኖረዋል እየተባለ ነው፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ የመተከል ጉዳይ እየተባባሰ በመምጣቱ የተፈናቃዮች ቁጥር ከ175 ሺ ዘሏል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply