መታገስ አዱኛ ጋርመንት የልብስ ስፌት በደብረታቦር ከተማ ስራ መጀመሩ ተገለፀ፡፡

መታገስ አዱኛ ጋርመንት የልብስ ስፌት በደብረታቦር ከተማ ስራ መጀመሩ ተገለፀ፡፡

መታገስ አዱኛ ጋርመንት የልብስ ስፌት በደብረታቦር ከተማ ስራ መጀመሩ ተገለፀ፡፡

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ሚያዝያ 5 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ

መታገስ አዱኛ ጋርመንት ወኪልና ስራ አስኪያጅ አቶ ሃብታሙ ምስጋናው እንደገለፁት 4ሺ ካሬ ሜትር ቦታ በ2ዐ11 ዓ/ም ተቀብለው 8 ሚዮን ብር ወጭ ግንባታውን በአጭር ጊዜ አጠናቅቀው ማሽኖችን አስገብተው በመብራት ምክንያት ወደ ስራ ሳይገቡ መቆየታቸውን ገልፀዋል፡፡

የነበረው የመብራት ችግር ተፈቶ ወደ ስራ የገቡ መሆኑንና ለ3ዐዐ ሰው የስራ እድል የሚፈጥረ እንደሆነ ገልፀው የተሰጣቸው ቦታ 3 መቶ ሰው መያዝ ስለማይችል መንግስት ተጨ ማሪ ቦታ ሰጥቷቸው ከዚህም በላይ ለብዙ ሰው የስራ እድል እንደሚፈጥሩ ገልፀዋል፡፡

የደቡብ ጎንደር ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ አባይነው ሃይሉ እንደገለፁት በደቡብ ጎንደር ዞን 3 የኢንዱስትሪ መንደሮች ያሉ ሲሆን በደብረታቦር ከተማ ልጅቱ ማርያም ኢንዱስትሪ መንደር 55 ፕሮጀክቶች ያሉ ሲሆን 7 ቱ ስራ ወደ ስራ የገቡ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በዛሬው እለት ስራ የጀመረው መታገስ አዱኛ ጋርመንት በአጭር ጊዜ ግንባታውን አጠናቆና ማሽኖችን አስገብቶ በመብራት ችግር ምክንያት ወደ ስራ ሳይገባ የቆየ መሆኑን ገልፀው በተደረገው ርብርብ መብራት ገብቶለት ወደስራ የገባ ሲሆን ለ3 መቶ ሰው የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይታሰባል ብለዋል፡፡

በስራ ላይ ያገኘናቸው ወ/ሪት ሁሉ አገሬ ሃይሌና ወ/ሪት የማታ ተረፈ እንደገለፁት ይህ ጋርመንት በመከፈቱ ለብዙ ሰው የስራ እድል ይፈጥራል እኛም ወደሌላ ቦታ ሳንሄድ በአካባቢያችን ሰርተን እንድንለወጥ ይረዳናል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በጉብኝቱላይ የተገኙት የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ ድርጅቱን ተዘዋውረው ከጎበኙ በኋላ ከመብራት ጋር የነበረው ችግር ተፈቶ ለዚህ በመብቃቱ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ድርጅቱ ጥራትና ብቃት ያለው ሰራተኛ ቀጥሮ ምርታማ እንዲሆን ሲሉ የገለፁ ሲሆን ብዙዎቹ ሰራተኞች ሴቶች በመሆናቸው ከቤተሰብ ጥገኝነት ወጥተው እራሳቸውን እንዲችሉ እድል ይፈጥራቸዋል ብለዋልበሲል የደቡብ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን ዘግቧል።


173102259 5268500463224531 5908447196087152391 n.jpg? nc cat=107&ccb=1 3& nc sid=730e14& nc ohc=2PGXV sBPXYAX b9MR3& nc ht=scontent dfw5 2
173898994 5268500476557863 5917688295445256648 n.jpg? nc cat=107&ccb=1 3& nc sid=730e14& nc ohc=AjqFiTAcJRQAX818Qsa& nc ht=scontent dfw5 2
173528350 5268500703224507 3909701430566840145 n.jpg? nc cat=107&ccb=1 3& nc sid=730e14& nc ohc=BskT8ZehO IAX9t8xXr& nc ht=scontent dfw5 2
Source:- አማራ ሚዲያ ማዕከል

Source: Link to the Post

Leave a Reply