You are currently viewing መነሻቸውን በጎንደር እና ጎጃም መስመር ያደረጉ ተጓዦች ካለፉት 6 ቀናት ጀምሮ በአፓርታይዱ አገዛዝ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ መከልከሉን ተከትሎ ለከፍተኛ ህክምና ሲመጣ የነበረ አንድ ሰው…

መነሻቸውን በጎንደር እና ጎጃም መስመር ያደረጉ ተጓዦች ካለፉት 6 ቀናት ጀምሮ በአፓርታይዱ አገዛዝ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ መከልከሉን ተከትሎ ለከፍተኛ ህክምና ሲመጣ የነበረ አንድ ሰው…

መነሻቸውን በጎንደር እና ጎጃም መስመር ያደረጉ ተጓዦች ካለፉት 6 ቀናት ጀምሮ በአፓርታይዱ አገዛዝ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ መከልከሉን ተከትሎ ለከፍተኛ ህክምና ሲመጣ የነበረ አንድ ሰው ህይወቱ አልፏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ መነሻቸውን በጎንደር እና ጎጃም መስመር ያደረጉ ተጓዦች ካለፉት 6 ቀናት ጀምሮ በአፓርታይዱ አገዛዝ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ መከልከሉን ተከትሎ ለህክምና ሲመጣ የነበረ አንድ ሰው ህይወቱ ማለፉን ተጓዦች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ገልጸዋል። ተጓዦች እንደሚሉት መንገዱ እንደ አዲስ ከሰሞኑ የተዘጋው ከየካቲት 1/2015 ጀምሮ ነው። በዚህም ምክንያት አማራዎች ጓህ ጽዮን ሲደርሱ ማለፍ አትችሉም በሚሉ የአቶ ሽመልስ አብዲሳ ታጣቂዎች ለከፍተኛ ስቃይ፣ እንግልት፣ ድብደባ እና እስር እየተዳረጉ መሆኑን መዳረጋቸውን ገልጸዋል። የካቲት 2/2015 ጀምሮ ከጎንደር ጎጃም መስመር ወደ አዲስ አበባ እንዳያልፉ ጓህጽዮን ላይ ከተከለከሉት መካከል ለህክምና እየመጡ ከነበሩት መካከል የአንደኛው ህይወት አልፏል። ሌሎች ሁለት ሰዎችም በከፍተኛ ህመም ላይ መሆናቸው ተገልጧል። በክልከላው ምክንያት በሽህ የሚቆጠሩ አማራዎች ደጀን ላይ ለተከታታይ 5 ቀናት ሲንገላቱ ከሰነበቱ በኋላ የካቲት 6/2015 ቢያንስ መንግስት ወደመጣንበት አካባቢ ሊመልሰን ይገባል ሲሉ ተማጽነዋል። በተመሳሳይ ከወሎ ደብረ ብርሃን አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድም ሸኖ ላይ እንዲሁም ከምንጃር ወደ አዲስ አበባ የሚመጡም በኦሮሞ አፓርታይዳዊ አገዛዝ ክልከላ የገጠማቸው በመሆኑ ለቀናት እየተሰቃዩ ሰንብተዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply