መነሻውን ከሻምቡ ዞን ያደረገ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ወደ ጃርዴጋ በማቅናት በዙሪያው ከበባ ማድረጉን ነዋሪዎች ገለጹ፤ ጭፍጨፋ ሊፈጽምብን ይችላል በሚል ከፍተኛ ሰጋት እንዳላ…

መነሻውን ከሻምቡ ዞን ያደረገ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ወደ ጃርዴጋ በማቅናት በዙሪያው ከበባ ማድረጉን ነዋሪዎች ገለጹ፤ ጭፍጨፋ ሊፈጽምብን ይችላል በሚል ከፍተኛ ሰጋት እንዳላቸው በመግለጽ የድረሱልን ጥሪም አቅርበዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 29 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ መነሻውን ከሻምቡ ዞን ያደረገ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ወደ ጃርዴጋ በማቅናት በዙሪያው ከበባ ማድረጉን ነዋሪዎች ገለጹ፤ ጭፍጨፋ ሊፈጽምብን ይችላል በሚል ከፍተኛ ሰጋት እንዳላቸው ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ገልጸዋል። የሁኔታውን አስፈሪነት የገለጹት ነዋሪዎች በአስቸኳይ የድረሱልን ጥሪ አቅርበዋል። በተደረጀው የአቶ ሽመልስ አብዲሳ ጦር ከበባ ውስጥ ካሉ አማራዎች መካከል አንዱ በውስጥ ያደረሰው መልዕክት የሚከተለው ነው:_ በሆሮጉዱሩ ወለጋ መነሻዉን ሻምቡ ከተማ ያደረገዉ ከ70 በላይ የሚሆን ልዩ ኃይል እና ሸኔ በጃርዴጋ እና ጃርቴ የሚኖሩ አማሮችን ለመጨፍጨፍ አሁን ጃርዴጋ ከተማን ከቧል። ህዝቡ ወደ ጫካ ገብቶ በርሀብ እና ጥም እየተሰቃዬ ነው። እናቶችም በወሊድ ምክንያት እየሞቱ ነዉ። በሻምቡ እና ጃርዴጋ ምሽግ ቆፍረዋል። በከባድ መሳሪያ ቤት እያቃጠሉ ነው። ህዝቡ ተከቦ ሞቱን እየተጠባበቀ ነው። አሁን የምፅፍላችሁ ድረሱልን ለማለት ሳይሆን እንድታውቁት ነው። ምክኒያቱም ከዚህ በኋላ ደርሶልን ከከበባ ያወጣናል የምንለዉ የለም። ለረጅም ጊዜ መከላከያ እንዲገባልን ስንለምን ቆይተን በመግባቱ ስንደሰት መከላከያ በዞኑ ዋና ከተማ ሻምቡ አሳራጆችን እንዲጠብቅ ተደርጎ ስንታረድ በጣም ያንገበግባል። ይህች የመጨረሻ መልክቴ ልትሆን ትችላለች። ከፈጣሪ ግን ተስፋ አንቆርጥም!

Source: Link to the Post

Leave a Reply