መንገድን በአግባቡ ባለመጠቀም ከ700 በላይ እግረኞች ተቀጡ፡፡

በመዲናዋ ትክክለኛ የመንገድ አጠቃቀም ያልተከተሉ ከ700 በላይ እግረኞች መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታውቋል።

ባለስልጣኑ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ በለሚ ኩራ፣ በጉለሌ በቦሌ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ የካ እና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች እና በሌሎች ቦታዎች የቁጥጥር ሥራ እንደተካሄደ በመግለፅ

በዚህም 777 እግረኞች የገንዘብና የማህበራዊ አገልግሎት ቅጣት ተላልፎባቸዋል ሲል ገልጿል።

የቁጥጥር ሥራው ከየክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ፣ ትራፊክ ፖሊስ፣ ደንብ ማስከበርና ሰላምና ፀጥታ ፅህፈት ቤቶች ጋር በመተባበር የተሰራ ስለመሆኑም ባለስልጣኑ ገልጿል።

ባለስልጣኑ በከተማዋ የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስም የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ እንደሆነም ጣቢያችን ከተላከለት መግለጫ ላይ ተመልክቷል።

በለዓለም አሰፋ

መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply