መንገዶች ላይ በግዴለሽነት ጉዳት እየደረሰ ነው—-የአዲስ አበባ ፖሊስበአዲስ አበባ ከተማ መንዶችን የማልማትና የማስዋብ ስራዎች በስፋት መከናወናቸው ይታወቃል፡፡ እነዚህን የልማት ስራዎችን…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/qqGJhEUFvWI2LWPLzlk1N2yoMXVCqQl0X-AoegG3z13nOmqxP3kLpS0vbDNVvQgn7JQP3sHAKb2sVx_zbS0AzoyP_E8aMZTMGyRMSsUgNJoeOGLJNMJFD4tedGQ7llD_DwK7ykLGmQNXUP4DKqMLWZl7sxLPp0ppkHq3DJnl3UHHCajtqVaDHmS9CP91Htpvz80XniLLBRxg1vLep4vYfoSVf-zajx3EJD4hfySLGlH20fUnMTJ-3k-dfYslpeRewCvO-0dxZUyaGzf3fNWujvb6hmC4A8o7JyZmVgjSDHjZ0-yMHO5INw30GOhHRMkSLjU-PZHuDs0xi3nrSRT9Vw.jpg

መንገዶች ላይ በግዴለሽነት ጉዳት እየደረሰ ነው—-የአዲስ አበባ ፖሊስ

በአዲስ አበባ ከተማ መንዶችን የማልማትና የማስዋብ ስራዎች በስፋት መከናወናቸው ይታወቃል፡፡

እነዚህን የልማት ስራዎችን መከባከብና መጠበቅ ሲገባ በግዴለሽነት በልማት ስራዎቹ ላይ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በሚደርስ አደጋ በሰውንና በንብረት ላይ ጉዳት እደረሰ ይገኛል፡፡ በአደጋው በሰዎች ላይ ከሚደርሰው ጉዳት በተጨማሪ ከፍተኛ ግምት ያለው ንብረት እየወደመ ይገኛል፡፡

የትራፊክ ፍሰቱን ለማሳለጥ እንዲያስችሉ ታቅዶ በርካታ ወጪ ወጥቶባቸው የተገነቡ የመሰረተ ልማት አውታሮች የአደጋው ሰለባ ከመሆን አላመለጡም ብሏል ፖሊስ፡፡

በመንግስትና በህዝብ ሐብት ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ የሚያደርገውን ጠንካራ ቁጥጥር ከማስቀጠል ጎን ለጎን ጉዳት ያደረሱ አሽከርካሪዎች ላይ የሚያደርገውን ምርመራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply