
“መንግሥታዊ እብደቱ ቀጥሏል፣ ሕዝባዊ ንቃቱም አይሏል!” አቶ ጌትነት ወርቁ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ጥር 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ዛሬ ጠዋት (ጥር 30) ኹሉም የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ሓላፊዎች( managers) በየቅርንጫፎቻቸው በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ስም የተከፈቱ አካውንቶችን አጣርተው (ያላቸውንም balance ይጨምራል) በአስቸኳይ እስከ ጠዋቱ 4:00 ብቻ እንዲያሳውቁ ተጠይቀዋል። ሌሎች ባንኮች ላይ መባሉን ማረጋግጥ አልቻልኩም። 1) ያው የመንግሥታዊ እብደቱ አካል ነው። 2) አካውንት እንዳይንቀሳቀስ ሊያግዱ ይችላሉ፤ ወይም እናግዳለን እያሉ ሊያስፈራሩ፤ 3) ከነገው (ረቡዕ) ፍርድ ቤት ቀጠሮ ጋር ሊገናኝ ይችላል፤ 4) ሌባ… ልጇን አታምነውም እንዲሉ ምን አልባት ቤ/ክርስቲያኗ ከውጭ ኃይሎች ጋር ግንኙነት አላት ብለው የሞኛሞኝ ሀሳብ አስበው፤ 5) ይሄ ኹሉ ሀብት የተገኘው ከእኛ “ወተትና ማር ከምታፈልቀው ምድር” ነው እያሉ ለማሸማቀቅ፤ ሕንድ ማላንካራውያን እና ሌሎች ላይ እንደሆነው “ብናካፍላቸው ስንት ይደርሳቸዋል?” በሚል(atleast ለመጎምዥት)፤ 6) ምን አልባት ቤተክርስቲያኗ በመንግሥት ውንብድና ክፉኛ ስለተቆጣች ብሯን አውጥታ ወደሌላ ባንክ ታሸሻለች ብሎ በመፍራት አጠቃላይ እንቅስቃሴውን ለማጥናት፤ ሌላም ሌላም ሊሆን ይችላል። መንግሥታዊ እብደቱ ቀጥሏል፣ ሕዝባዊ ንቃቱም አይሏል!
Source: Link to the Post