“መንግሥት ህወሓት እየሠራ ያለውን ግፍና በደል ሊቀለብስ የሚችል ሥራ እየሠራ አይደለም” – ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ

ህወሓት እየሠራ ያለው ግፍና በደል በጣም ሰፊ ቢሆንም የፌዴራል መንግሥት ይህንን ሊቀለብስ የሚችል ሥራ እየሠራ አይደለም ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝም ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ አስታወቁ። ‹‹በጉዳዩ የፌዴራል መንግሥት ብዙ ጊዜ ጥያቄና ወቀሳ ቀርቦበታል። ዝምታው ግን ለምን እንደሆነ አይገባኝም።በተለይም የትግራይ ክልል የተደራጀ ኃይል ያለው እንደመሆኑ ያንን መመከት የሚያስችል እንቅስቃሴ እየተደረገ አይደለም›› ብለዋል። – ዝምታው ህዝቡ እንዳይጎዳ ከማሰብ የተነሳ ቀስ በቀስ አመራሩን ማዳከም የፈለገ እንደሚመስል በመጠቆምም፤ ሂደቱ በአንድ በኩል ትክክል ነው። ነገር ግን አንድ ቦታ ላይ ከሚወሰደው ዕርምጃ አኳያ አድሎ ሊመስል እንደሚችል አመልክተዋል። የቀድሞ የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ መሀመድ ኡመር በሱማሌ ክልል ችግር በፈጠረበት ጊዜ ወዲያውኑ ዕርምጃ መወሰዱን

The post “መንግሥት ህወሓት እየሠራ ያለውን ግፍና በደል ሊቀለብስ የሚችል ሥራ እየሠራ አይደለም” – ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ appeared first on ዘ-ሐበሻ Ethiopian Latest News & Point of View 24/7.

Source: Link to the Post

Leave a Reply