መንግሥት በሶማሌ ክልል ብዙ ግፍና በደል ሲፈፅሙ የነበሩትን የከሃዲውን የሕወሓት አባላት በቁጥጥር ስር በማዋል ለሕግ እንዲያቀርብ ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ህዳር 24 ቀን 2013…

መንግሥት በሶማሌ ክልል ብዙ ግፍና በደል ሲፈፅሙ የነበሩትን የከሃዲውን የሕወሓት አባላት በቁጥጥር ስር በማዋል ለሕግ እንዲያቀርብ ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 24 ቀን 2013…

መንግሥት በሶማሌ ክልል ብዙ ግፍና በደል ሲፈፅሙ የነበሩትን የከሃዲውን የሕወሓት አባላት በቁጥጥር ስር በማዋል ለሕግ እንዲያቀርብ ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የሶማሌ ክልል ከሃዲው ሕወሓት ስልጣኑን ተቆጣጥሮ ለበርካታ ዓመታት በህዝብ ላይ የለየለት ግፍና በደል እንዲሁም ዝርፊያ ሲፈፅምባቸው ከነበሩ ክልሎች አንዱ ነው። የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት በከሃዲው የህወሓት ቡድን ላይ በተቀዳጀው ድል መደሰታቸውን ተናግረዋል። አያይዘውም መንግሥት በሶማሌ ክልል ብዙ ግፍና በደል ሲፈፅሙ የነበሩትን የጁንታውን አባላት በቁጥጥር ስር በማዋል ለሕግ እንደሚያቀርብ ያላቸውን እምነት የገለፁት ነዋሪዎች በሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ የተመራው የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በፋፈን፣ ጀረር እና ዶሎ ዞኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ጉብኝት ማድረጉን ተከትሎ ነው። ለ13 ቀናት የተካሄደው ጉብኝትና ህዝባዊ ኮንፍረንስ ከዚህ ቀደም በመንግስት ተዘንግተው የቆዩና ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያዋስኑ የጠረፍ አካባቢዎችን ታሳቢ ያደረገ ስለመሆኑ ተነግሯል። ጉብኝቱ የየማኅበረሰቡን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ ስራዎችን ለመስራት ያግዛል ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሀመድ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በክልሉ የሰፈነውን ሰላም ተከትሎ ህዝቡ ሰፊ የመሰረተ ልማት ጥያቄ ማንሳቱን ተናግረዋል። በጉብኝቱ ወቅት የጋሻሞ ደሮር ሎት 1 የ140 ኪ.ሜ የጠጠር ጥርጊያ መንገድ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠ ሲሆን በጀረር ዞን የአቦከር ት/ቤት የማስፋፊያ ፕሮጀክት እና የጋሻሞ ሆስፒታል ተመርቀዋል። ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ በየአካባቢው ባደረጓቸው ህዝባዊ ኮንፍረንሶች ላይ ህዝቡ የተገኘውን ሰላም በመጠበቅ ረገድ የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል። ዜናውን ለማጠናቀር ኤፍ ቢ ሲን በምንጭነት ተጠቅመናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply