መንግሥት በትህነግ ላይ የወሰደውን ሕግ የማስከበር ርምጃ በሌሎች አካባቢዎችም መድገም እንዳለበት በወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ በቃፍቲያ ሁመራ ወረዳ የአምባ ድር ኩታን (አዲ ጎሹ) ከተማ ነ…

መንግሥት በትህነግ ላይ የወሰደውን ሕግ የማስከበር ርምጃ በሌሎች አካባቢዎችም መድገም እንዳለበት በወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ በቃፍቲያ ሁመራ ወረዳ የአምባ ድር ኩታን (አዲ ጎሹ) ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 8 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ ዞን በቃፍቲያ ሁመራ ወረዳ የአምባ ድር ኩታን (አዲ ጎሹ) ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። ሰላማዊ ሰልፉ መንግስት ህግ ለማስከበር የወሰደውን ርምጃ ለመደገፍና የአካባቢው ህዝብ ለረዥም ዓመታት ሲጠይቁት የነበረውን የማንነትና የወሰን ጉዳይ እንዲረጋገጥ የሚጠይቅ ነው። ማንነታችን አማራ፣ ደምበራችን ተከዜ፣ መሬቱም የአማራ ነው፣ መንግስት ይህን አውቆ ውሳኔ መስጠት እንዳለበት በሰላማዊ ሰልፉ ገልጸዋል። አስተያየታቸውን ለአብመድ የሰጡ የሰልፉ ተሳታፊዎች የህወሃት ቡድን ከአሁን በፊት ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃትና የሰብአዊ መብት ጥሰት ያደርስባቸው እንደነበር አስታውሰው መንግስት በትህነግ ላይ የወሰደውን ሕግ የማስከበር ርምጃ በሌሎች አካባቢዎችም እንዲቀጥል ጠይቀዋል። ህግን ለማስከበር እልህ አስጨራሽ ትግል ላደረጉ የመከላከያ ሠራዊት የአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ ምስጋና አቅርበዋል ሲል አብመድ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply