መንግሥት በትግራይ ክልል ያለ ፈቃድ በተንቀሳቀሱ የተመድ ሠራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱ ተሰማ፡፡                አሻራ ሚዲያ          ህዳር…

መንግሥት በትግራይ ክልል ያለ ፈቃድ በተንቀሳቀሱ የተመድ ሠራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱ ተሰማ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር…

መንግሥት በትግራይ ክልል ያለ ፈቃድ በተንቀሳቀሱ የተመድ ሠራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱ ተሰማ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-30/3/13/ዓ.ም ባህር ዳር ከተፈቀዱላቸው የመንቀሳቀሻ ሥፍራዎች ውጪ በመሄድ ሦስተኛ ኬላ ሊጥሱ ሲሞክሩ የነበሩ የተመድ ሠራተኞች ላይ የፀጥታ ኃይሎች እርምጃ መውሰዳቸው ተገልጻል፡፡ እነዚህ ያለፍቃድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት የተመድ ሰራተኞች መታሰራቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገልጸዋል፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዳራሽ በወቅታዊ ጉዳዮችና በትግራይ ክልል ባለው የሰብዓዊ ዕርዳታ ሥርጭት ላይ ከብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ጋር በመሆን መግለጫ የሰጡት አምባሳደር ሬድዋን እነዚህ ሰዎች እንዲንቀሳቀሱ ከተፈቀደላቸው ሥፍራ ውጪ ለመንቀሳቀስ ባደረጉት ሙከራ ሁለት ኬላዎችን ጥሰው ከሄዱ በኋላ ሦስተኛውን ለመጣስ ሲሞክሩ እርምጃው እንደተወሰደባቸው አስታውቀዋል፡፡ አምባሳደር ሬድዋን ይኼ ሕግ አልባና ባለቤት አልባ አገር አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ ያልተገደበ መንቀሳቀሻ የሚባል ነገር በፍፁም የለም ሲሉም አስረድተዋል፡፡ አገሪቱ መንግሥት ያላትና በሰሜኑ ክፍል ብቻ ችግር የገጠማት ሆና ሳለ እነዚህ የተመድ ሠራተኞች መግባት የማይገባቸው ሥፍራ እንዳለ ተነግሯቸው ነበር ብለዋል፡፡ በእርዳታ ስም ውጊያ ቀጠና ውስጥ የገቡት ፈረንጆች ዓላማቸው ጁንታውን ሰብስበው ጭነው ለመውጣት ነበር። ሰሞኑን ሰብአዊ እርዳታ እያሉ የከረሙትየተመድ ሠራተኞች ዋና ዓላማቸው ለጁንታው ማምለጫ ቀዳዳ ለማግኘት እንደነበር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናግረዋል። ይህች ኢትዮጵያ መሆኗ በግልጽ መታወቅ ይኖርበታል፡፡ በሺዎች ዓመታት የሚቆጠሩ የአገርነት ልምድ ያላት አገር ናት፡፡ ማንም እንዳሻው መሆን አይችልም፡፡ አትሂዱ ከተባሉ አለመሄድ ነው ያለባቸው፡፡ ነገር ግን ሰራተኞቹ የመንግሥትን ማሳሰቢያ ችላ በማለትና በማናለብኝነት የመንግስትን ትዕዛዝ በመጣሳቸው እርምጃው ተወስዶባቸዋል ሲሉ በትዕላንትናው ዕለት መግለጻቸው ይታወሳል ፡፡ ይህንንም አስመልክቶ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ጋር እንደገና ውይይት መጀመሩ ተገልጻል፡፡ ከተወሰኑት የሚከተለውን አደረግሁ ባቸው። ግን ዪትዩቡ ሪዳይሬክት አያረግም ዘወትር አዳዲስ መረጃ እንዲደርስዎ https://t.me/asharamedia24 በመጫን ይቀላቀሉን። ዩትዩብ፥ https://bit.ly/33XmKro ላይክ እና ሰብስክራይብ ያድርጉን ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply