መንግሥት በትግራይ የሰብዓዊ እርዳታን የሚያስተጓጉል ችግር የለም አለ – BBC News አማርኛ

መንግሥት በትግራይ የሰብዓዊ እርዳታን የሚያስተጓጉል ችግር የለም አለ – BBC News አማርኛ

https://ichef.bbci.co.uk/news/1024/branded_amharic/BAFD/production/_115996874_mediaitem115996873.jpg

በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ ለማቀረብ የሚደረገው ጥረት በውጊያ ምክንያት እንደተስተጓጎለ የሚነገር እውነት እንዳልሆነ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ገለጸ። ጽህፈት ቤቱ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው በክልሉ በሚገኙ “በርካታ ከተሞችና በዙሪያቸው ባሉ አካባቢዎች በሚካሄድ ውጊያ የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራው እንቅፋት እንደገጠመው ተደርጎ የሚነገረው ሐሰት” እንደሆነ ገልጾ ይህም በአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት ክልሉን ለማረጋጋት የተከናወኑ ወሳኝ ተግባራትን የሚቃረን ነው ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply