መንግሥት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ ከሚሊሻ ጋር የተፈጠረውን ክስተት በቅርበት እየተከታተለ ነው – ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

መንግሥት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ ከሚሊሻ ጋር የተፈጠረውን ክስተት በቅርበት እየተከታተለ ነው – ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)መንግሥት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ ከሚሊሻ ጋር የተፈጠረውን ክስተት በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡

ችግሮችን ለመፍታት ሁሌም ውይይትን የምንጠቀም በመሆኑ እንዲህ ያሉ ክስተቶች የሁለቱንም ሀገራት ትስስር አያላሉም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፡፡

እንደ መልካም አጋጣሚ ወስደው በማራገብ ልዩነትን ለማስፋት የሚጥሩ አካላት የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ትስስር ያልተረዱ ናቸው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

የታሪካዊ ግንኙነታችንን ጥንካሬ በግልጽ አለመረዳታቸውንም ነው የገለጹት ፡፡

The post መንግሥት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ ከሚሊሻ ጋር የተፈጠረውን ክስተት በቅርበት እየተከታተለ ነው – ዶ/ር ዐቢይ አህመድ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply