You are currently viewing መንግሥት በኢንተርኔት ግንኙነት ላይ የጣለውን ገደብ እንዲያነሳ ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     የካቲት 24 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲስ አበባ ሸዋ መንግሥት በኢንተርኔት…

መንግሥት በኢንተርኔት ግንኙነት ላይ የጣለውን ገደብ እንዲያነሳ ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 24 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ መንግሥት በኢንተርኔት…

መንግሥት በኢንተርኔት ግንኙነት ላይ የጣለውን ገደብ እንዲያነሳ ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 24 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ መንግሥት በኢንተርኔት ግንኙት ላይ የጣለው ገደብ ሚዲያዎች ላይ ተጽእኖ እየፈጠረ በመሆኑ፣ ገደቡ እንዲያነሳ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት የካቲት 24/2015 ባወጣው መግለጫ ጠይቋል፡፡ ምክር ቤቱ በመግለጫው፣ መንግሥት በአንዳንድ የማኅራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች ላይ የጣለው ገደብ መገናኛ ብዙሃን መረጃ የማሰባሰብ፣ የማደራጀት እና ለሕዝብ ተደራሽ የማድረግ ሥራቸው ላይ ተግዳሮት ፈጥሯል ብሏል፡፡ በተለይ ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የሚዲያ ሥራ በሚሰሩ ሚዲያዎች ላይ የፈጠረው ተጽእኖ ከፍተኛ መሆኑን ምክር ቤቱ ጠቁሟል፡፡ መገናኛ ብዙኃን ሥራቸው በአግባቡ ለሕዝብ ተደራሽ እንዳያደርጉ እንቅፋት የሆነው የኢንተርኔት ገደብ እንዲሳ ምክር ቤቱ ጠይቋል፡፡ አገልግሎቱ የተቋረጠባቸው የማኅበራዊ ሚዲያዎች ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ቲክቶክ እና ሜሴንጀር ሲሆኑ፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ችግር ጋር በተገናኘ መንግሥት በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የኢንተርኔት ገደብ ከጣለ 20 ቀናቶችን አስቆጥሯል ሲል የዘገበው አዲስ ሪፖርተር ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply