መንግሥት ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር ያደረጋቸው የሰላም ድርድሮች ያልተሳኩት ቡድኑ “አገር አፍራሽ” አጀንዳዎችን ይዞ በመቅረቡ እንደኾነ የኦሮሚያ ክልል ኮምንኬሽን ቢሮ ሃላፊ ኃይሉ አዱኛ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/aZdu8vTr4H3PtEpWquqynZr3H-9HAo-et8x-OLKqcwZMNd7nvVF1RItUIPvLZ1jDapCakT10V5wAFuftPV7NJTdizkxKuibvw0ZmHHVsYYE2EqsnNtAax8bALszjH9FZF-Q-ACKRq7G5lnEHa3eJjFBzxfLCzj6BcAcGZdMwcmnFWq8NfPjcysQH--BFhMzXpOWfU1tl3fC15kRpmyXK1PbknliiH6buOup7svf-gfBgZpfbxvdf1w48wK_6UWi_ls3MX6DmP5gzIHwcwfabYWEfaOCsbruaBVCFcU6bxz_s3Z6RVLjsPGiOnMClMMQGkW_PMTddhHgR24axt02Eyg.jpg

መንግሥት ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር ያደረጋቸው የሰላም ድርድሮች ያልተሳኩት ቡድኑ “አገር አፍራሽ” አጀንዳዎችን ይዞ በመቅረቡ እንደኾነ የኦሮሚያ ክልል ኮምንኬሽን ቢሮ ሃላፊ ኃይሉ አዱኛ ተናግረዋል።

ካኹን ቀደም ታንዛኒያ ላይ በተደረጉ ኹለት ድርድሮች፣ አማጺው ቡድን ያቀረባቸው አጀንዳዎች ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን የሚንዱ እና አገራዊ አንድነትን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡ እንደነበሩ የገለጡት ኃይሉ፣ አጀንዳዎች መንግሥት ሊደራደርባቸው የማይችሉ “ቀይ መስመሮች” እንደኾነ ገልጸዋል።

የኮምንኬሽን ቢሮ ኃላፊው፣ አማጺው ቡድን የድርድር አጀንዳዎቹን ቀይሮ ከቀረበ ግን መንግሥት ለሌላ ዙር የሰላም ድርድር ዝግጁ መኾኑን ጠቁመዋል።

አማጺው ቡድን፣ የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እጃቸውን ለመስጠት የሞከሩ በርካታ ታጣቂዎቹን እንደገደለ የክልሉ መንግሥት መረጃ እንዳለውም ኃላፊው ጠቅሰዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply