መንግሥት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሱዳን ላይ ጥቃት ሰነዘረ የሚለው ክስ መሰረተ ቢስ ወሬ ነው አለ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 19 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ…

መንግሥት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሱዳን ላይ ጥቃት ሰነዘረ የሚለው ክስ መሰረተ ቢስ ወሬ ነው አለ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 19 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የትኛውም ሉኣላዊ አገር ላይ ጥቃት የመፈፀም አጀንዳ የለውም ሲል መንግሥት አስታውቋል። በወቅታዊው የኢትዮጵያ ሁኔታ ጫና ለማሳደር እየሰሩ የሚገኙ የውጭ አገራት መገናኛ ብዙኃን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሱዳን ላይ ጥቃት እንደሰነዘረ የሚገልፁ የፈጠራ ወሬዎችን ሲያሰራጩ ታይተዋል። አገር ለማፍረስ በተያዘው ሴራ ከአሸባሪዎችና አጋሮቻቸው ጎን ቆመው በተናበበ ዘመቻ ኢትዮጵያን እየወጉ የሚገኙት እንደእነ ሲኤንኤን፣ ሮይተርስ፣ ቢቢሲና ሌሎችም መገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች ባለፈው ሳምንት በሱዳን መንግሥት ቀለብ እየተሰፈረላቸው ሲዶልቱ እንደነበር ይታወሳል። ዓላማቸው ደግሞ ኢትዮጵያ ላይ ተጨማሪ ጫና የሚያሳድሩ ሀሰተኛ ወሬን ለመፈብረክ መመካከር እንደነበር ኬንያዊው የፀጥናታ ደኅንነትን ተንታኝ ማጋለጣቸው ይታወሳል። ከሰሞኑም እነዚህ መገናኛ ብዙኃን ኢትዮጵያ ሱዳን ላይ ጥቃት እንደፈፀመች አድርገው የፈጠራ ዘገባን እያሰራጩ ይገኛል። ከእነዚህ ዘገባዎች ጋር በተያያዘ በኢቲቬ በኩል ማብራሪያ የሰጡት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) “አሸባሪው ኃይል በተለያየ መልኩ ሱዳን ውስጥ የሚያሰለጥናቸውን ሰርጎ ገቦች በተለያየ ቦታ በተለይም በመተማ አካባቢዎች በተለያየ ጊዜያት ያስገባል” ብለዋል። በዚህም በተለያየ ጊዜ ኢትዮጵያን የሚተናኮሉ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰርጎ ገቦች፣ ሽፍታዎች እና አሸባሪዎች በመተማ መስመር ገብተው እንደነበር፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የአካባቢው ሚሊሻም እንደደመሰሷቸው አሳውቀዋል። በመሆኑም የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እንደሚነዙት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሱዳን ጦር ላይ ጥቃት አልፈፀመም፤ መሰረተ ቢስ ነው ያሉት ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የትኛውም ሉኣላዊ አገር ላይ ጥቃት የመፈፀም አጀንዳ የለውም ብለዋል። መንግሥት ይህ ፍላጎት ቢኖረው ኖሮ የሱዳን ኃይሎች ወረው በግድ የያዙት የኢትዮጵያ መሬት እንዳለ በማስታወስ መንግሥት በውይይትና ሰላማዊ መንገድ እንፈተለን ብሎ እንደተቀመጠ አፅንኦት ሰጥተዋል። አሸባሪው ሕወሓት አገር ለማፍረስ በሚያደርገው እንቅስቃሴ አንዱ መጠቀሚያ ያደረገው ከሱዳን በኩል እየገባ ጥቃት ለማድረስ መሞከር ሲሆን ይህን የመመከት ግዴታ ያለበት የኢትዮጵያ መንግሥት በግዛቱ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን እየቀለበሰና ሰርጎ ገብ ሽፍታዎችን እየደመመሰሰ ይገኛል። ይህ ደግሞ ፅንፈኞቹ መገናኛ ብዙኃን እንደሚሉት ሱዳን ላይ ጥቃት ተሰነዘረ የሚያስብል አመክንዮን የሚፈጥርበት አንዳችም ምክንያት የለውም ስለመባሉ ዋልታ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply