You are currently viewing መንግሥት ጥቁር ልብስ የለበሱ ሰዎችን ማሰር እና መደብደብ እንዲያስቆም ኢሰመጉ ጠየቀ          ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም           አሻራ ሚዲያ ፣  የፌደራል መንግሥት እና የኦሮ…

መንግሥት ጥቁር ልብስ የለበሱ ሰዎችን ማሰር እና መደብደብ እንዲያስቆም ኢሰመጉ ጠየቀ ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የፌደራል መንግሥት እና የኦሮ…

መንግሥት ጥቁር ልብስ የለበሱ ሰዎችን ማሰር እና መደብደብ እንዲያስቆም ኢሰመጉ ጠየቀ ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የፌደራል መንግሥት እና የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የጸጥታ ኃይሎች፣ በቤተክርስቲያን እውቅና ያልተሰጣቸውን ኤጲስ ቆጶሳትን የተቃወሙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ላይ የሚፈጽሙትን ግድያ፣ ድብደባ እና እስር እንዲያቆሙ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ጠይቋል፡፡ ከቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ በተላለፈው መልእክት መሰረት፣ ጥቁር ልብስ የለበሱ ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ እስሮች እና ድብደባዎችን ይቁሙ ሲል ኢሰመጉ በዛሬው ዕለት ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ አሳስቧል፡፡ ከሕግ አግባብ ውጪ ግድያ፣ እስራት፣ ደብደባ እና ሌሎችም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች የፈጸሙ የጸጥታ አካላትን መንግሥት በሕግ ተጠያቂ እንዲያደርግም ጠይቋል፡፡ ጉዳዩ መፍትሄ እንዳያገኝና ወደ ግጭት እንዲቀየር ለማድረግ ነገሮችን ወደ ሌላ አቅጣጫ የሚስቡ አካላት ሁሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉም፣ ኢሰመጉ በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል፡፡ ኢሰመጉ ባወጣው ወቅታዊ መግለጫ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ጋር ተያይዘው የሚነሱ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮችን ሲከታተል መቆየቱን አስታውቋል። ተቋሙ ጥር 14/2015 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ባልተሰጣቸው ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት አማካኝነት 26 ኤጲስ ቆጶሳት መሾማቸውን አስታውሷል። ቅዱስ ሲኖዶሱ ሕገ-ወጥ ያላቸው አካላት፣ በመንግሥት የጸጥታ አካላት ጭምር ታጅበው ወደ አብያተክርስቲያናት መግባታቸው ኢሰመጉ የጠቆመ ሲሆን፤ ምዕመኑም ይህንን ባለመቀበሉ ምክንያት በተፈጠሩ ግጭቶች፣ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ተፈጽመዋል ብሏል፡፡ በዚህም በሻሸመኔ ከተማ ከመንግሥት የጸጥታ አካላት በተተኮሱ ጥይቶች የሰዎች ህይወት ማለፉን፣ የአካል ጉዳት መድረሱን በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡ እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች በቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ላይ ጭምር እስራት፣ ማዋከብ እና ድብደባ መፈጸሙን ኢሰመጉ ተረድቻለሁ ብሏል፡፡ ይህንን አካሄድ በተቃወሙ የእምነቱ ተከታዮች ላይ እና የቤተክርሲቲያኒቱ አገልጋዮች ላይ ድብደባዎች እንደተፈጸሙ፣ ቤት ሰብሮ በመግባት የሕግ ሥነ ስርዓትን ያልተከተሉ እስራቶች እንደተከናወኑና በርካታ ቁጥር ያለቸው ሰዎችም በብዛት እየታሰሩ መሆኑንም ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት መቻሉን ገልጿል፡፡ ከቅዱስ ሲኖዶሱ በተላለፈ መልዕክት መሰረት፤ ጥቁር ልብስ የለበሱ ሰዎችን በአንዳንድ አካባቢዎች እስራት፣ እንግልት እና መዋከብ እየተፈጸመባቸው እንደሆነና ይህንንም ድርጊት አንዳንድ ተቋማት እና ድርጅቶች በተመሳሳይ መልኩ እየፈጸሙት መሆኑን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት መቻሉንም አስታውቋል፡፡ ስለሆነም ችግሩ ተባብሶና ተስፋፍቶ ተጨማሪ ጥፋት ከማስከተሉ በፊት፣ የሚመለከታቸው አካላት ኹሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የበኩላቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ኢሰመጉ ጥሪውን አቅርቧል፡፡ ሃይማኖት የማኅበራዊ መስተጋብር አንዱ ክፍልና መብት መሆኑን ያነሳው ኢሰመጉ፤ መንግሥት የማኅበረሰቡን ሰላማዊ እንቅስቃሴ የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበት በመረዳት የፌደራል እና የክልል መንግሥታት የዜጎችን ደህንነት እንዲያስከብሩ ጠይቋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply