You are currently viewing መንግሰት እንደ አቅጣጫ ይዞ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2015 ዓ.ም የሚጀምረዉ የተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ቅሬታ ቀረበበት!       ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም          አሻራ…

መንግሰት እንደ አቅጣጫ ይዞ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2015 ዓ.ም የሚጀምረዉ የተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ቅሬታ ቀረበበት! ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ…

መንግሰት እንደ አቅጣጫ ይዞ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2015 ዓ.ም የሚጀምረዉ የተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ቅሬታ ቀረበበት! ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ተማሪዎቹ ‹ በዩኒቨርስቲያቸው የተዘጋጀላቸዉን የመዉጫ ፈተና ለመውሰድ ሲዘጋጁ እንደቆዩ › ገልጸው ‹ ለመፈተን ጥቂት ጊዜ ሲቀራቸው ትምህርት ሚኒስቴር በላከዉ መረጃ ፈተናዉ አገር አቀፍና ወጥ ነዉ ማለቱ ግር አሰኝቶናል › ብለዋል፡፡ ‹ አሁን ላይ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ለተመሳሳይ የትምህርት ክፍል በድጋሜ ለመውጫ ፈተና ተዘጋጅቶ የተሰጡን የኮርስ አይነቶች አንዱ ዩኒቨርስቲ የወሰዳቸው፣ ሌላዉ ግቢ ደግሞ ጭራሽ ያልተማራቸዉ ሆነዉ አግገኘተናቸዋል › ባይ ናቸዉ፡፡ ‹ ይሄንንም ከተለያዩ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋር ባደረግነዉ የመረጃ ልውውጥ ለማወቅ ችለናል › ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለተመሳሳይ የት/ት ክፍል ወጥ አገር አቀፍ የመዉጫ ፈተና እንደተዘጋጀ መግለፁን የሚያስታውሱት ተማሪዎቹ የመዉጫ ፈተና ኮርሶች አንድ አይነት ባለመሆናቸዉ ግር እንዳሰኛቸው ገልፀዋል፡፡ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት፣ አካዉንቲግ፣ቱሪዝም ቅሬታ ከቀረበባቸዉ የትምህርት ክፍሎች መካከል ይገገኙበታል፡፡ አሻም የተማሪዎቹን ቅሬታ መነሻ በማድረግ የግልጽነት ጥያቄ በቀረበበት የመውጫ ፈተና ዙሪያ ጉዳዩ የሚመለከተዉን የትምሕርት ሚኒስቴርን በአካል፣ በስልክና በአጭር የፅሁፍ መልክት በተደጋጋሚ ምላሽና ማብራሪያ ለማሰጠት ብትሞክርም ፍቃደኛ ባለመሆኑ በዘገባው ሊካተት አልቻለም፡፡ ሚኒስቴሩ ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ በሆነበት አፍታ የምታስተናግድ ይሆናል፡፡ በ2015 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ለዩኒቨርሰቲ ተመራቂ ተማሪዎች የተዘጋጀዉ የመዉጫ ፈተና በመጪው ሰኞ ከሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሰጥ ሚኒስቴሩ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply