You are currently viewing መንግስታዊ መዋቅርን በመጠቀም የዘር ማጥፋት ወንጀልን የፈፀመ ስርዓት የሀገር ህልውናን ማስቀጥል አይችልም! ሰ.አሜሪካ:- ሰኔ 19/2014 ዓ.ም                    አሻራ ሚዲያ መ…

መንግስታዊ መዋቅርን በመጠቀም የዘር ማጥፋት ወንጀልን የፈፀመ ስርዓት የሀገር ህልውናን ማስቀጥል አይችልም! ሰ.አሜሪካ:- ሰኔ 19/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ መ…

መንግስታዊ መዋቅርን በመጠቀም የዘር ማጥፋት ወንጀልን የፈፀመ ስርዓት የሀገር ህልውናን ማስቀጥል አይችልም! ሰ.አሜሪካ:- ሰኔ 19/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ መንግስት ዝቅተኛ ግደታው የዜጎችን #ደህንነት መጠበቅ መሆኑ ግልፅ ነው። እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ሆኖ ሰብአዊ ውድመት ሆኖ ይገኛል። ህዝባችንን ለዘመናት ያስገደለውን አሮጌ ስርዓት አሺቀንጥሮ ካልጠላ ዘር ተኮር ጭፍጨፋው ተባብሶ የሚቀጥል መሆኑ እየታየ ነው። የአማራ ህዝብ ችግር ከፓርቲ በላይ ነው። የመዳኛ መንገዱ ደግሞ ግልፅ የሆነ #አብዮታዊ ትግል ነው። አማራን በየጊዜው ዕረፍት የሚነሳውን ድርጅት ከነ ግሳንግሱ አሺንቀንጥሮ ለመጣል ሁሉንተናዊ ትግልን ማጠናከር የግድ ነው። በህዝባችን ላይ የነበረውን አጉል የጀብደኝነት ባህል ወደ መሬት ማውረድ የሁላችንም ሰብአዊ ግደታ ነው። ህዝባችን ነባር የሆነ የትግል ዕሴቱን ይከተል።ነፍጠኝነት መለያ ባህሪይው ለሆነ ህዝብ የትኛውንም የህይወት ዋጋ ከፍሎ ህዝቡን ከዘር ፍጅት ሰለባ ማውጣት አለበት። በየትኛውም ሁኔታ ለህዝብ የማይመጥኑንና ሞቱን የማይቀንሱ ነገሮችን በማድረግ ጊዜ ማባከን አይጠቅምም። የተከታታይ ዓመት መንግስታዊ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ በአንድ ሰሞን ጩኸት የሚመለስ አይደለም። መድረሻችንና መዳኛ መንገዳችንን ከጥሬ ስልጣንና ምኞት መውጣት አለበት። አማራ በሃገራዊ አበርክቶ ያደረገውን ተጋድሎ ኢትዮጲያና ኢትዮጲያውያን ትንሺ ቅርጭጭት ውስጥ አስገብተውታል።ሞታችንን ጭምር እየተሳለቁበት ነው። ስለዚህ ከጊዚያዊ የፓለቲካ ድብታና ፍርሃት መውጣት የግድ ነው። በተለይም የምንከፍለውን ዋጋ የሃገሪቱ ዜጎች በጣም ርካሺ መስዋአትነት አድርገው ከቆጠሩት የግድ ወደ ራሳችን መመልከት አለብን። ህዝባችን ከነበረው አጉል ተስፍኝነት ወጥቶ የራሱን #አማራ ሪፐብሊክ እስከ መመስረት የሚሄድ የትግል አብዮትን ማዋለድ አለበት። እየፈረሰ ባለ ህንፃ ውስጥ የአማራ #ኢትዮጲያዊነት የቂል ፓለቲካ ነው። ለዘመናት ይዘነው የነበረውን ፓለቲካል ኮምፕሮማይዝም ውጤት አልባ ሆኖ ለገዳዮቻችን ጉልበት እየሆነ ነው።በዚህ መንገድ የነበረውን ድፕሎማቲክ እይታ ማስተካከልም ብልህነት ነው። በተለይ #በነጮቹ ላይ የተሰራውን ዕሳቤ መቀየርም አስፈላጊ ተግባር ነው።#ነጮቹ በአማራው ላይ ያላቸውን የተዛባ ፓለቲካዊ አመለካከት ማስተካከል የግድ ነው። ታሪክ ከማበላሸት ጋር ተያይዞ የሚነሳውን መሰረታዊ ያልሆነ አምክንዩ አሺቀንጥሮ መጣልም የግድ ነው። አማራ የራሱን ሪፐብሊክ መመስረት ከቻለ ከየትኞቹም ሃይሎች ጋር ተደራዳሪ ሆኖ ይኖራል። ግብ የሌለው ፓለቲካን ማራገብ በታቀደ መንገድ እየሰሩ ያሉ ሃይሎችን ፍላጎት የሚያስደነግጥ አይሆንም!! በፓርቲ ስም ተጠልላችሁ የምትኖሩ የአማራ ባለስልጣናት በመሸ ጊዜም ቢሆን ራሳችሁን ብትገመግሙ ጥሩ ነው። በጊዚያዊ ስልጣን የህዝብን ጥቅም አሳልፎ መስጠት እና ህዝብን በመናቅ የዜጎችን ህልውና ከሰብአዊነት ባነሰ መልኩ አረማዊ ድርጊት እየተፈፀመባቸው ማየት ሰወኛ ባህሪይም አይደለ!!! አማራን በማሳደድ የሚፀና መንግስታዊ መዋቅርም የለም። ሁሉም በጊዜው ይሆናል። የመጨረሻውን ሳቅ እኛው የምንስቅ ይሆናል!! #በቃ! #እምቢ! #AmharaGenocide! © አሸናፊ ገናን ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply