You are currently viewing መንግስት ለትንሳኤ በዓል መዋያ እንኳ ድጋፍ አላደረገልንም ሲሉ በቱሉጋና የሚገኙ ተፈናቃዮች ተናገሩ፤ በአንጻሩ አንድ ባለሀብት ሁለት በሬ ገዝተው ስላበረከቱልን ድጋፍ እናመሰግናለን ብለዋል።…

መንግስት ለትንሳኤ በዓል መዋያ እንኳ ድጋፍ አላደረገልንም ሲሉ በቱሉጋና የሚገኙ ተፈናቃዮች ተናገሩ፤ በአንጻሩ አንድ ባለሀብት ሁለት በሬ ገዝተው ስላበረከቱልን ድጋፍ እናመሰግናለን ብለዋል።…

መንግስት ለትንሳኤ በዓል መዋያ እንኳ ድጋፍ አላደረገልንም ሲሉ በቱሉጋና የሚገኙ ተፈናቃዮች ተናገሩ፤ በአንጻሩ አንድ ባለሀብት ሁለት በሬ ገዝተው ስላበረከቱልን ድጋፍ እናመሰግናለን ብለዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ወንድምነው ጸጋዬ ነዋሪነታቸው በሆሮ ጉድሩ ዞን አቢ ደንጎሮ ወረዳ ቱሉጋና ሲሆን ከተለያዩ አካባቢዎች በአማራዊ ማንነታቸው ተፈናቅለው በቱሉጋና ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚገኙ ከአንድ ሺህ ላላነሱ ተፈናቃይ ወገኖች በግል ተነሳሽነት ሁለት በሬዎችን በመግዛት የትንሳኤ በዓልን በመልካም ስሜት እንዲያከብሩ አድርገዋል ተብሏል። ተጎጅዎች እንደሚሉት መንግስት ለትንሳኤ በዓል አንድም የሰብአዊ እርዳታ አለማድረጉ ቢያሳዝነንም ወንድማችን አቶ ወንድምነው ጸጋዬ ሚያዝያ 16/2014 ሁለት በሬ በማረድ ለእያንዳንዳችን አንድ አንድ ኪሎ ስጋ በማደል በዓሉን በደስታ እንድናሳልፍ አድርጓል ብለዋል። ከዚህ በተቃራኒው በዘረኝነት አስተሳሰብ አዕምሯቸው የታወሩ ሲሉ ብዙዎች ያወገዟቸው የአቢ ደንጎሮ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ብሪሳ ኃይሌ ግን በአቢ ደንጎሮ ለተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆች ብቻ ሀምሳ ሀምሳ ኪሎ ስንዴ እና የፍርኖ ድቄት ሲያድሉ የአማራ ተፈናቃዮችን ለይተው ትተዋል፤ በዚህ አሳዛኝ ተግባራቸውም ማፈር ይገባቸዋል ብለዋል። ዘረኛ አካሄድን እንጠየፋለን ያሉት የቱሉጋና ነዋሪዎች አቶ ብሪሳ ኃይሌ ከአሁን ቀደምም በጫካ ካለው ከኦነግ ሸኔ ጋር ተባብረው ጥቃት እንዲፈጸም ሲያደርጉ መክረማቸውን አውስተዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply