መንግስት ለኢትዮ ሱዳን ድንበር ጉዳይ ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ በቅድሚያ ወርዶ ተጎጅ ወገኖችን ማነጋገር ብሎም በኃላፊነት ስሜት፣ ለዘላቂ መፍትሄ መታገል አለበት ሲል ፖለቲከኛ አግባው ሰጠኝ ተ…

መንግስት ለኢትዮ ሱዳን ድንበር ጉዳይ ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ በቅድሚያ ወርዶ ተጎጅ ወገኖችን ማነጋገር ብሎም በኃላፊነት ስሜት፣ ለዘላቂ መፍትሄ መታገል አለበት ሲል ፖለቲከኛ አግባው ሰጠኝ ተ…

መንግስት ለኢትዮ ሱዳን ድንበር ጉዳይ ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ በቅድሚያ ወርዶ ተጎጅ ወገኖችን ማነጋገር ብሎም በኃላፊነት ስሜት፣ ለዘላቂ መፍትሄ መታገል አለበት ሲል ፖለቲከኛ አግባው ሰጠኝ ተናገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 18 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በተቃውሞ ጎራው ተሰልፎ ለረዥም ዓመታት ሲታገል ቆይቷል፤ ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ ነው የፓርቲ ፖለቲካ ተሳትፎ ያደረገው። በ1997 ዓ.ም ምርጫም ቅንጅትን በመወከል ተወዳድሮ አሸንፎ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አገልግሏል። ይህ ብቻ አይደለም፤ አንድነት ፓርቲ ሲቋቋም መስራች ነበር፤ ከአንድነት ወጥቶ ሰማያዊ ፓርቲ ሲመሰረትም የፓርቲው መስራችና የማዕከላዊ ኮሚቴና በሰሜን ጎንደር ዞን የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሆኖ ሰርቷል_ፖለቲከኛ አግባው ሰጠኝ። የአማራ ሚዲያ ማዕከል ከሰሞኑ ወደ ጎንደር ባቀናበት ወቅት ስለኢትዮ ሱዳን ድንበር ጉዳይ በም/ቤት ውስጥ ሆኖ ጭምር ከፍተኛ ትግል ሲያደርግ ከነበረው ከፖለቲከኛ አግባው ሰጠኝ ጋር አጠር ያለ ቆይታ አድርጓል። አግባው ሰጠኝ በህይወቱ ከገጠሙት ፈተናዎች መካከል አንዱ የሱዳን ወረራን እና የመንግስትን ዝምታ፣ አለፍ ሲልም መሬት ላይ ያለውን እውነታ የማድበስበስ አካሄድን በም/ቤት ውስጥ ሆኖ በግልፅ በመቃወሙና በማጋለጡ የተነሳ ተደጋጋሚ የመግደል ሙከራ ተደርጎበታል። ለፖለቲካ ትርፍ ሲል የኢትዮጵያን ሉአላዊ መሬት አሳልፎ ለሱዳን የሸጠው ትሕነግ መራሹ መንግስት በሱዳን ጉዳይ በአደባባይ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ውስጥ ሳይቀር ሲዋሽ እንደነበር ተገልጧል። በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ምክንያት በተደጋጋሚ ለአስከፊ እስር እና እንግልት ከተዳረጉት መካከል አንዱ የሆነው አግባው ሰጠኝ ሉአላዊ ግዛትን ለሱዳን አሳልፎ የሰጠው ሟቹ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ተጠያቂ መሆኑን በአደባባይ የተናገረ ነው። የኢትዮጵያ ገበሬዎች መሬታቸው ለሱዳን ተላልፎ ተሰጥቶ በገዛ መሬታቸው ከሱዳን ተከራይተው እንዲያርሱ የተደረገበት ጊዜ እንደነበርም አውስቷል። ሰሊጥ፣ማሽላ፣ጥጥ እና ሌሎች ሰብሎች በስፋት የሚመረቱበት ከቋራ እስከ ምዕራብ አርማጭሆ፣ ማይካድራና ሁመራ ያለው ለም መሬት ለሀገር ኢኮኖሚ ዋና መሰረት መሆኑ ይታወቃል ያለው አግባብ አሁን ላይ የሱዳን ጦር ሰፊ የኢትዮጵያን መሬት መቆጣጠሩን ገልጧል። ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መንግስት በትሕነግ ላይ ህግ የማስከበር እርምጃ ላይ ባለበት ወቅት ይህን እንደ መልካም አሀኘጋጣሚ በመጠቀም የሱዳን ጦር ያደረገው ወረራ የተለዬ እና ከበስተጀርባው የሶስተኛ ወገን እጅ እንዳለበት አመላካች ነው ብሎ እንደሚያምን ነው የገለፀው_አግባው ሰጠኝ። መንግስት በትሕነግ ላይ እርምጃ ሲወስድ ድንበሩን ክፍት ማድረጉ ተገቢ አልነበረም ሲል ወቅሷል። መንግስት ጦርነቱ አላስፈላጊ ነው ብሎ ካመነ እንኳ ቢያንስ በሱዳን ጦር የተዘረፉ ባለሀብቶችን እና አርሶ አደሮችን ወርዶ ማነጋገር ነበረበት ያለው አግባው አሁን ላይ የሱዳን ጦር በመተማ ደለሎ፣ በስናር፣ በምዕራብ አርማጭሆ ገላሉባን፣ወዲቁራ፣ ኮረደምና በሌሎችም አካባቢዎች ያለምንም መከላከል ገብቶ ሰፊ መሬት ይዟል ብሏል። በምድረ ገነት ከተማ አካባቢ ሰላም በር ብቻ ነው መከላከል ተደርጎ እንዲመለሱ ሳይሆን ባሉበት እንዲቆሙ ለማድረግ የተቻለው ሲልም አክሏል። በተለይ አደገኛ በሆነው የትሕነግ ገዳይ ስርዓት ወቅት እንኳ ትናንት ገበሬው በአንድ እጁ ጠመንጃ በሌላኛው እጁ እርፍ ይዞ ተናንቆ አስከብሮት የቆየውን መሬት ዛሬ ላይ በሱዳን የተያዘበት መሆኑን ጠቅሷል። አግባው ሰጠኝ አሁን ያለው የሱዳን እንቅስቃሴ ከመሬት ጥያቄ ያለፈ ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጧል። በመጨረሻም መንግስት ለኢትዮ ሱዳን ድንበር ጉዳይ ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ በመጀመሪያ ደረጃ ወርዶ ተጎጅ ወገኖችን ማነጋገር ብሎም ተወረናል ብሎ ላመነው ችግር በኃላፊነት ስሜት በመታገል ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ መስራት አለበት ሲል አሳስቧል። ወደሱዳን የኮበለሉት የትሕነግ ነፍሰ ገዳዮች ከጠላት ጋር እያበሩ በተለያዩ አካባቢዎች ጉዳት እያደረሱ በመሆኑ መንግስት በልዩ ሊመለከተውና ለዘላቂ ሰላም እንዲሰራ ሲል ነው አግባው ጥሪ ያቀረበው። ከፖለቲከኛ አግባው ሰጠኝ ጋር በጎንደር ከተማ ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply