መንግስት መር በሆነው የጃርዴጋ እና አካባቢው የአራት ቀናት ጦርነት በግፍ የተገደሉት አማራዎች ስም ዝርዝር በከፊል ደርሶናል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 12 ቀን 2015 ዓ/ም…

መንግስት መር በሆነው የጃርዴጋ እና አካባቢው የአራት ቀናት ጦርነት በግፍ የተገደሉት አማራዎች ስም ዝርዝር በከፊል ደርሶናል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 12 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ከተለያዩ ታማኝ ምንጮች እንዳጣራው መንግስት መር በሆነው የጃርዴጋ እና አካባቢው የአራት ቀናት (ማለትም ህዳር 13፣ህዳር 29፣ ህዳር 30 እና ታህሳስ 1/2015) ጦርነት በግፍ ከተገደሉት በርካታ አማራዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል። (1)_ከህዳር 29/2015 ጀምሮ፣ ህዳር 30 እና ታህሳስ 1/2015 በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ጃርዴጋ እና አካባቢው:_ 1) በኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ 2) በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ፣ 3) በሽምቅ ተዋጊዎች (ሪጴሎላ)፣ 4) በስርዓቱ ጋሻ (ጋቼና ሲርና)፣ 5) በፖሊሶች፣ 6) በሚሊሾች እና 7) በተደራጁ ቄሮዎች በቅንጅት ለተከታታይ ሶስት ቀናት በተደረገው የወረራ ጦርነት ራሳቸውን፣ ህጻናትንና ሴቶችን ሲከላከሉ ብሎም ለማምለጥ ሲሸሹ ከተገደሉት ከ30 በላይ አማራዎች ስም ዝርዝር:_ 1) ሙሉጌታ ገደፋው፣ 2) ሞላ በላይ፣ 3) ከማል አለባቸው፣ 4) አደም መሀመድ፣ 5) ኢብራሂም በድሩ፣ ታህሳስ 1/2015 ሰምቦ ለጋ ፈርሶ ላይ ከእነ ነፍሱ በእሳት ተቃጥሎ የተገደለ እና አጥንቱ ታህሳስ 10/2015 ተገኝቶ ስርዓተ ቀብሩ ተፈጽሟል። የሚያሳዝነው አሊማ በድሩ የተባለች እህቱም ከመስከረም እስከ ጥቅምት 2015 ልክ እንደ እነ:_ 1) መዲና ሁሴን፣ 2) መሬም ዳውድ እና 3) ፋጡማ ወንድምነው በጃርዴጋ በህክምና እጦት ህይወቷ ማለፉ ይታወሳል። 6) ኢብራሂም ገዜ፣ 7) አህመድ ወርቁ ይመር፣ አባቱ አቶ ወርቁ ይመር ማለት ጃርዴጋ ላይ ኬላ እየጠበቁ ሳለ ያለምንም ጥፋታቸው ወደ ጃርቴ ተወስደው ከአንድ ወር በላይ ከታሰሩ በኋላ መስከረም 12/2015 በጃርቴ እስር ቤት እያሉ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ የተገደሉ ናቸው። በእለቱም በአማራዊ ማንነታቸው ከእስረኛ ተለይተው በአሰቃቂ መልኩ ከተገደሉት በርካታ አማራዎች መካከል ወርቁ ይመርን ጨምሮ:_ 1) ሰይድ ይሃ፣ 2) ኑሬ አህመድ እና 3) መሀመድ ወርቁ ይገኙበታል። 8 ጋሻው ኡመር፣ 9) የሱፍ ጋሻው፣ 10) ልዬው ክብረት፣ 11) ኡመር አደም፣ 12) ሱሌማን ወርቁ፣ 13) ተሾመ በላይ፣ 14) ወለላው ዘለቀ፣ 15) ፋጡማ ሰይድ፣ 16) አህመድ ይመር፣ 17) አደም ሰይድ፣ 18) በላይ በለጠ፣ 19) ፈንታው በለጠ፣ 20) ዳውድ አራጌ፣ 21) ፈቀደ በለጠ፣ 22) መሀመድ እስሌማን እና 23) የኑስ አደም የተባሉ ነዋሪዎች ይገኙበታል። ከህዳር 29/2015 ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በጃርዴጋ ላይ በተደረገው የወረራ ጦርነት ከቆሰሉት ከ40 በላይ አማራዎች መካከል:_ 1) ማሞ ጋሻው፣ (የተገደለው የአቶ የሱፍ ጋሻው ወንድም) 2) ዘይን ኡመር፣ 3) ሰይድ ሀሩን፣ 4) ሀሺም ጎርፉ፣ 5) ክንዱ ስጦታው፣ (በከባድ)፣ 6) አወል ተመቸው፣ የአቶ ተመቸው ቃሲም ኢብራሂም ልጅ፣ 7) አህመድ በድሩ ዳውድ፣ 8 ደሴ በላይ፣(በከባድ)፣ 9) ኡመር አሰፌ፣ 10) ሰይድ ስሜነው፣(በከባድ የቆሰለ)፣ 11) ደሴ አወቀ፣ 12) ጋሻው፣ 13) አብዱ በድሩ፣ 14) ተሹ ገሰሰ፣(በከባድ የቆሰለ)፣ 15) መሀመድ ቃሲም፣ በሸኔ የተገደሉት የአቶ ቃሲም ኢብራሂም ልጅ፣ 16) ቻሌ (በከባድ የቆሰለ)፣ 17) መሀመድ ወርቁ፣ 18) ተሾመ አበበ እና 19) አህመድ የተባሉ ነዋሪዎች ይገኙበታል። በተመሳሳይ ህዳር 13/2015 በጃርዴጋ ሹልኬ በተባለ ኬላ ላይ በግፍ የተገደሉ አማራዎች:_ 1) ሰይድ አለም፣ ከአሁን በፊት አባቱ አቶ አለም ይብሬ እና አጎቱ ቃሲም ይብሬ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ በግፍ የተገደሉበት ሲሆን እሱም ለ7 ወራት በኦህዴድ እስር ቤት ሲሰቃይ የቆዬ ጀግና እንደነበር ተገልጧል። 2) ጦይብ አለም፣ 3) መሀመድ ጅብሪል፣ 4) አዳነ አሰፌ እና 5) ኢሳ አሕመድ ይጠቀሳሉ። በጥቃቱ ከቆሰሉት መካከልም:_ 1) አሕመድ ይመር፣ 2) ሐብቴ ስጦት፣ 3) ወርቁ በዜ እና 4) ደጉ መኮንን የተባሉ ነዋሪዎች ይገኙበታል። በዚህ አረመኔያዊ ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ የተገደሉት እና የቆሰሉት አማራዎች ከደረስንባቸው በላይ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። አሁን ላይም በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ራሳቸውን ከመንግስት መር ጥቃት ለማትረፍ በጃርዴጋ የገጠር መንደሮችና በየጫካው እየተንከራተቱ መሆኑ ይታወቃል። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ ከጥቃት የተረፉ ነዋሪዎች ኢሰመጉ፣ኢሰመኮ እና የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ሲቪክ አደረጃጀቶች የሚመለከተው የመንግስት አካል በየጫካው እየተንከራተቱ በርሃብ እየተሰቃዩ ላሉ ወገኖች በተለያዩ ጊዜያት የድረሱላቸው ጥሪ ቢያሰሙም የሚደርስላቸው አካል እንዳልተገኘ በእጅጉ ባዘነ፣ በተሰበረ እና ተስፋ በቆረጠ ልብ ይናገራሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply