መንግስት ሰብዓዊ መብቶችን እንዲያከብር ተጠየቀ።መንግስት ሰብዓዊ መብቶችን የማክበርና የማስከበር ህገ-መንግስታዊ ሀላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ አይደለም ሲል የመብቶችና ዲሞክራሲ ዕድገት ማዕከ…

መንግስት ሰብዓዊ መብቶችን እንዲያከብር ተጠየቀ።

መንግስት ሰብዓዊ መብቶችን የማክበርና የማስከበር ህገ-መንግስታዊ ሀላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ አይደለም ሲል የመብቶችና ዲሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (CARD) አስታውቋል።

የዛሬይቱ ኢትዮጵያ የዘፈቀደ ግድያ፣የጅምላና ህጋዊ መሠረት ያሌላቸዉ እስሮች፣ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች፣የአካል ጉዳተኞች ፤ እኩልነት የተነፈጉ አሰራሮችና ሌሎችም በርካታ ሰብዓዊ መብቶች ተጥሶባታል ሲሉ የመብቶችና ዲሞክራሲ ዕድገት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ በፍቃዱ ሀይሉ ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ ይህንን የተናገሩት በትላንትናው ዕለት በካፒታል ሆቴል 75ኛዉ የሰብዓዊ መብቶች ቀን በተከበረበት ዕለት ነዉ።

በዕለቱም በሰብዓዊ መብቶች ላይ ሲሰለጥኑ የቆዩ 191 የሁለተኛ ደረጃና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የምረቃት መርሀ ግብር ተካሂዷል።

በመላዉ ዓለም በትላንናዉ ዕለትም ዲሴምበር 10, 75ኛዉ የሰብዓዊ መብቶች ቀን የተከበረ ሲሆን “ነፃነት፣እኩልነትና ፍትህ ለሁሉም” በሚሉ መሪ ቃል ተከብሯል።
የመብቶችና ዲሞክራሲ ዕድገት ማዕከልም ለሰብዓዊ መብቶች በጋራ እንቁም በማለት ቀኑን ያሰበ ሲሆን ለሁለት ቀናት ያሰለጠናቸዉን 191 ተማሪዎች አስመርቋል።

የመብቶችና ዲሞክራሲ ዕድገት ማዕከል ሰብዓዊነት በኢትዮጵያ እንዲሰፍን እና እነዚህን በህግ የተደነገጉ ሰብዓዊ መብቶችም በተግባር እንዲጠበቁ እየታገልን” ነዉ ሲሉም ተናግዋል።
ስለሆነም አዲሱ ትዉልድ በይበልጥ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባውን የሰብዓዊ መብት ተሞጋቾችን ቁጥር በመቀላቀል ለሰብዓዊ መብቶች መከበር መስራት እንደሚገባ መልዕክታቸዉን ለወጣቶች አስተላልፈዋል።

በአቤል ደጀኔ

ታህሳስ 01 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ
መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8)

Source: Link to the Post

Leave a Reply