መንግስት በህክምና ዘርፍ ለተመረቁ ባለሙያዎች የስራ ዕድል ባለመፍጠሩ በሀገሪቱ ህሙማን ተገቢውን አገልግሎት እንዳያገኙ ሆኗል ተባለ፡፡በሀገሪቱ በቂ የሆነ የህክምና ባለሙያ አለመኖሩ ቢገለፅም…

መንግስት በህክምና ዘርፍ ለተመረቁ ባለሙያዎች የስራ ዕድል ባለመፍጠሩ በሀገሪቱ ህሙማን ተገቢውን አገልግሎት እንዳያገኙ ሆኗል ተባለ፡፡

በሀገሪቱ በቂ የሆነ የህክምና ባለሙያ አለመኖሩ ቢገለፅም በዘርፉ ስራ አጥተው የተቀመጡ የጤና ባለሞያዎች መኖራቸው ተነግሯል።

በህክምና ባለሙያ እጥረት ቀጠሮ የሚሰጠው የማህበረሰብ ክፍል የመብዛቱን ያክል በዘርፉ ተመርቀው ስራ ያጡ የህክምና ባለሙያዎች እንዳሉ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ፕሬዝዳንት ዶክተር ተግባር ይግዛው ለኢትዮ ኤፍም ተናግረዋል።

ማህበረሰቡ በቂ ህክምና እያገኘ እንዳልሆነ በማንሳት ምክንያቱ ደሞ በቂ ሀኪም በሀገሪቱ አለመኖሩ እንደሆነ አንስተዋል።

በዚህም ሳቢያ ማህበረሰቡ በሀኪም እጥረት ምክንያት የተፈለገውን ህክምና እንደማያገኝ እና በቀጠሮ እንደሚንገላታ ሰምተናል

ከዚህ ጋር በተያያዘም በዘርፉ የሚወጡ ጥናቶች እንደሚያሳዩትም ድንገተኛ ተካሚዎች እንኳን ሳይቀር በቀጠሮ ህክምና እንደሚደረግላቸው ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።

በቂ ሀኪም በሀገሪቱ እንደሌለ ያነሱት ሀላፊው ይሁን እንጂ አሁንም በሺዎች የሚቆጠሩ ሀኪሞች ስራ እንዳልያዙ ተናግረዋል።

ብዙ የህክምና ተቋማት በከተማ እንደሚገኙ ተነስቶ ከገጠሩ ማህበረሰብ የሚመጣ ታካሚ በዙውን ጊዜ በቀጠሮ እንደሚንገላታምተነግሯል።

በኢትዮጵያ ህክምና ተምረዉ የተመረቁ ዶክተሮች ቁጥር ወደ 17ሺህ አከባቢ እንደሆነ ከዚህ ቀደም ጣቢያችን መዘገቡ የሚታወስ ነው።

በለአለም አሰፋ

መጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply