መንግስት በመተከል የተለያዩ ወረዳዎች በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ ተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰባቸው ያሉ ወገኖቻችን ለመታደግ እንድንገባ ይፍቀድልን ሲሉ ትሕነግን ለመደምሰስ በተለያዩ የግዳጅ ቀጠናዎ…

መንግስት በመተከል የተለያዩ ወረዳዎች በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ ተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰባቸው ያሉ ወገኖቻችን ለመታደግ እንድንገባ ይፍቀድልን ሲሉ ትሕነግን ለመደምሰስ በተለያዩ የግዳጅ ቀጠናዎ…

መንግስት በመተከል የተለያዩ ወረዳዎች በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ ተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰባቸው ያሉ ወገኖቻችን ለመታደግ እንድንገባ ይፍቀድልን ሲሉ ትሕነግን ለመደምሰስ በተለያዩ የግዳጅ ቀጠናዎች የተሳተፉ ፋኖዎች ጠየቁ። አሻራ ሚዲያ ህዳር 30/2013 ዓ•ም ባህርዳር ወደመተከል እንግባ ያሉት የፋኖ አመራሮችና አባላት መካከል አርበኛ ገበየሁ እንየው ይገኝበታል። አርበኛ ገበየሁ እንየውና በርካታ የፋኖ አደረጃጀትና አባላት መንግስት በአሸባሪው ትሕነግ ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ በመደገፍ ከአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ አባላት በተጨማሪ በቀዳሚነትና በፈቃደኝነት ተሰልፈው አያሌ ምሽጎችን በመደርመስና እብሪተኛውን ትሕነግን በመደምሰስ የድል ባለቤት ከሆኑት መካከል አንዱ ነው። አርበኛ ገበየሁ እና መሰሎቹ የመጀመሪያ ጠባችን በአማራ ህዝብ ላይ ተደጋጋሚ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ ያለው የአሸባሪውን ትሕነግን እብሪት በማስተንፈስ የአማራ አፅመ እርስቶችን ማስመለስ መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል። እነ አርበኛ ገበየሁ በጠለምትና በአዳርቃይ እንደ አብነትም በማይጠብሪ፣በማይለሃምና በሌሎች አካባቢዎችም ተሰልፈው ጠላትን በመደምሰስ የታፈኑ ወገኖቻችን ነጻ በማድረግ የራሳቸውን ታሪካዊ አሻራ ማሳረፋቸውን ተናግረዋል። አሁን ላይም በመተከል የተለያዩ ወረዳዎች በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለውን አሳዛኝ የጅምላ ግድያ፣እገታ፣አፈና እና ማፈናቀልን ለማስቆም ፈቃደኛ መሆናችን አውቆ መንግስት ጥሪ እንዲያደርግልን እንፈልጋለን ብለዋል። የመተከል አማራ እጣ ፈንታ ጉዳይ ከጊዜ ወደ ጊዜ አሳሳቢ እየሆነ ቢመጣም መንግስት የችግሩን ስፋት ተገንዝቦ በመቀልበስ ረገድ ግን ከፍተኛ ውስንነት ያለበት መሆኑን በመገንዘባችን ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት አካባቢውን ከአፈና እና ጭቆና ነጻ ለማውጣት ወትሮ ዝግጁ መሆናችን በይፋ እናሳውቃለን ሲሉ ገልፀዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል እንደዘገበው!

Source: Link to the Post

Leave a Reply