መንግስት በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ እና ምዕራብ አርማጭሆ በኩል የሱዳን ጦር በተደጋጋሚ እያደረገ ባለው ትንኮሳ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን በመገንዘብ ለችግሩ እልባት እንዲሰጥ ተጠየቀ። አማራ…

መንግስት በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ እና ምዕራብ አርማጭሆ በኩል የሱዳን ጦር በተደጋጋሚ እያደረገ ባለው ትንኮሳ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን በመገንዘብ ለችግሩ እልባት እንዲሰጥ ተጠየቀ። አማራ…

መንግስት በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ እና ምዕራብ አርማጭሆ በኩል የሱዳን ጦር በተደጋጋሚ እያደረገ ባለው ትንኮሳ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን በመገንዘብ ለችግሩ እልባት እንዲሰጥ ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአንድ ወቅት “ከአማራ ይልቅ ሱዳን ይሻለናል” ሲሉ የተናገሩት የአሸባሪው ትሕነግ መሪ ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገ/ሚካኤል ቡድኑ የበታችነት ስሜቱን፣የሀሰት ትርክትና ጥላቻውን በማኒፌስቶውና በመዋቅሩ አካቶ በአማራ ላይ ሲፈፅመው እንደነበር ከንግግራቸው ለመረዳት ይቻላል። በምዕራብ ጎንደር ዞን በቋራ፣በመተማና በምዕራብ አርማጭሆ በኩል በተለያዩ ጊዜያት የሱዳን ጦር በሚያደርገው የመስፋፋት፣የግድያና የዝርፊያ ወንጀሎች ከትሕነግ የተላኩ ታጣቂዎች ስለመሳተፋቸው መረጃ አለን ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች መናገራቸው ይታወሳል። በሽብርና በጅምላ የዘር ፍጅት ተሰማርቶ የኖረው የትሕነግ/ ሕወሓት ቡድን አመራር እነ አቶ አባይ ፀሀዬ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ከሱዳን ጋር በመመሳጠር የኢትዮጵያን ሉአላዊነትን በማስደፈር መሬት መሸጣቸው የተመሰከረ ጉዳይ ነው። አሁን ላይ ለዘመናት ወጥሮ የያዛቸው እብሪትና ድንቁርናቸው በአማራ ልዩ ሀይል፣በፋኖ፣በሚሊሻውና በመከላከያ ሰራዊት እንዲተነፍስና እንዲሟሽሽ በተደረገበት ወቅትም ተስፋ ቆራጮቹ ማይካድራ ላይ ከ700 በላይ አማራዎችን በጅምላ ጨፍጭፈው ወደ ሱዳን መጠጋታቸው ይታወቃል። የመተማና የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ነዋሪዎችም የነገሩን በሱዳን የተጠጋው ትሕነግ በጥላቻ አውሮ ያሰማራው ነፍሰ ገዳይ ቡድን ሳምረ፣ልዩ ሀይሎችና ሚሊሻዎች ከቻሉ ከሱዳን ጦር ጋር ሆነው ላለመውጋታቸው፣ ካልቻሉም ገንዘብ እየረጩ በሱዳን ጦር በኩል ጉዳት ማስከተላቸው አይቀርም ይላሉ። በቅርቡም በምዕራብ አርማጭሆ መሰረት መቅረት መቅረጫና በወዲ ከውሊ እንዲሁም በመተማ ደለሎ ቁጥር 3 በኩል የሱዳን ጦር በሚያደርሰው ትንኮሳ ጉዳት እየደረሰ ነው ብለዋል። በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ጠረፍ ወርቅ በተባለ ቀበሌ በኢንቨስትመንት የተሰማሩት ባለሀብት አቶ ድረስ ካሳ አሁን ላይ ወቅቱን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ትንኮሳ በማድረግ የደረሰ ሰብል እንዳይሰበሰብ እያደረጉ ነው፤ ከዝርፊያው በተጨማሪም የቀንድ ከብቶችን ከጓንግ ወንዝ ውሃ እንዳናጠጣም እየከለከሉ ነው ብለዋል። እንደአብነት ሲጠቅሱም መሰረት መቅረጫ ላይ ባለሀብት አቶ ይርጋ ሽቤን በማፈናቀል የእርሻ ካምፑን ይዘዋል፤ በተጨማሪም በጠረፍ ወርቅ ወዲ ከውሊ አካባቢም የእነ አቶ ሰለሞን በየነን ማሽላን በመቁረጥ በጋሬ እያሻገሩ ስለመሆኑ እየተነገረ ነው ብለዋል። የአሸባሪው ትሕነግ እጅ እንዳለበት መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ ያሉት አቶ ድረስ ከአሁን ቀደም የነበረውን ተሳትፎአቸውንም ጠቁመዋል። አስራት ሲሳይ፣ገብሬ ዘመነና ታዴ ውብነህ በሱዳን ጦር ከካምፓቸው ተወስደው ከወራት የአፈና ቆይታ በኋላ ነሀሴ 24 ቀን 2012 ዓ.ም በመተማ ኢሚግሬሽን በኩል አምጥተው ያስረከቧቸው መሆኑንም አውስተዋል። ዋናው ጠላታችን ሱዳን ሳይሆን ትሕነግ ነው ያሉት አቶ ድረስ ቸልተኝነት አያስፈልግም፤ መንግስትም ሆነ ህዝቡ ነቅቶ አካባቢውን መጠበቅና ሉአላዊነቱን ማስከበር አለበት የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። በተመሳሳይ በምዕራብ አርማጭሆ ጠረፍ ወርቅ/ ኮርሁመር አካባቢ በእርሻ ልማት የተሰማራውን የአቶ ጋሻው እንዳልክን የእርሻ ካምፕ እና ትራክተሮች በሱዳን ጦር የተቃጠለበት መሆኑን አሚማ ከሳምንታት በፊት መዘገቡ ይታወሳል። በመተማ የደለሎ ባለሀብት የሆኑት አቶ ዮሀንስ ተስፋዬ የሱዳን ጦር በደለሎ አካባቢ ያልተለመደ እንቅስቃሴ እያሳየ ነው ይላሉ። እንደአብነትም በደለሎ ቁጥር 3 አካባቢ የባለሀብት አቶ አደራጀውንና የሌሎች አርሶ አደሮችን ማሽላ እየቆረጡ ከመውሰዳቸው ባሻገር በዶዘር ምሽግ እየቆፈሩ ጦር ሲያስጠጉ ይስተዋላልም ብለዋል። የሱዳን ወታደሮች በዝርፊያ ላይ ተሰማርተዋል ሲሉ የገለፁት አቶ ዮሃንስ ባለፈው ዓመት 30 የቁም ከብቶችን ወስደው አርደው እንደበሉባቸው አውስተዋል። ወታደሮቹ መንግስት አላቸው ለማለት ይቸግረኛል ያሉት አቶ ዮሃንስማህበረሰቡ ግን አብሮ መኖር የሚፈልግ መሆኑን አውቃለሁ ብለዋል። ወደ ሱዳን ከሸሹት የትሕነግ ወንጀለኞች አኳያም በአካባቢው ጠንከር ያለ ስራ መሰራት እንዳለበት፣ ወንጀለኞችን ለመያዝም ከሱዳን ጋር የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ማሳደግ ተገቢ ስለመሆኑ ተናግረዋል። ከባለሀብቶቹ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ የምናጋራ ይሆናል። ፎቶ:መኮንን እዘዘው/Mekonen Ezezew Mckonnen

Source: Link to the Post

Leave a Reply