You are currently viewing መንግስት በሰላም ተጠናቀቀ ባለው የጥምቀት በዓል አከባበር በርካታ ንጹሃን ሰዎች በጸጥታ አካላት ስለመገደላቸው መረጃዎች አመለከቱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ጥር 14 ቀን 2015 ዓ/…

መንግስት በሰላም ተጠናቀቀ ባለው የጥምቀት በዓል አከባበር በርካታ ንጹሃን ሰዎች በጸጥታ አካላት ስለመገደላቸው መረጃዎች አመለከቱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 14 ቀን 2015 ዓ/…

መንግስት በሰላም ተጠናቀቀ ባለው የጥምቀት በዓል አከባበር በርካታ ንጹሃን ሰዎች በጸጥታ አካላት ስለመገደላቸው መረጃዎች አመለከቱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 14 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ መንግስት በሰላም ተጠናቀቀ ሲል የጥምቀት በዓል አከባበርን በተመለከተ ሪፖርት ማቅረቡ ይታወሳል። ይሁን እንጅ ዘግየት ብሎ እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንዳመለከቱት በተለያዩ አካባቢዎች ከጸጥታ አካላት በተተኮሰ ጥይት የበርካታ ንጹሃን ህይወት ማለፉንና የቆሰሉ ስለመኖራቸው መረጃዎች አመልክተዋል። የጥምቀት በዓልን ተከትሎ በጥይት ከተገደሉት መካከል ከአዘዞ በቅርብ ርቀት በሚገኘው ድርማ ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም አስተዳዳሪ አባ ኪዳነ ማርያም እና ሌሎች ሁለት መነኮሳት ጉዳይ የመጀመሪያ ተጠቃሽ ነው። መረጃዎች እንዳመለከቱት ጥር 12/2015 የቅዱስ ሚካኤልን ታቦት ወደ መንበሩ በሰላም አስገብተው አመሻሹን እየተመለሱ ሳለ በአደባባይ በጥይት እሩምታ ተመተው ተገድለዋል። እነዚህን የቤተ-ክርስቲያን አገልጋይ አባቶች ማን እና ለምን ፍላጎትና አላማ እንደገደላቸው በትክክል ለማወቅ አልተቻለም። በተመሳሳይ በዳባት ወረዳ የጥምቀት እለት 2:30 ገደማ አንድ በጥምቀት በዓል የደስታ ጥይት ተኩሷል የተባለ ወጣት ከልዩ ኃይል አባል በተተኮሰ ጥይት መገደሉ ታውቋል። ይህ ብቻ ሳይሆን በዘንድሮው የጥምቀት በዓል አከባበር በአለፋ ጣቁሳ ወረዳ ደልጊም የጸጥታ አካላት ጥይት በመተኮስ አንድ ወጣት ገድለዋል፤ 6 ሌሎች ወጣቶችንም አቁስለዋል። በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ማርያም ሰፈር አካባቢም ታቦት አስገብተው ሲመለሱ በነበሩ ወጣቶች ላይ የአካባቢው የፖሊስ አባላት ጥይት በመተኮስ ቢላል ታዴ የተባለ ወጣትን ሲገድሉ ሌሎች 4 ወጣቶችን አቁስለዋል። ከመካከላቸው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ጥቁር አንበሳ እና አቤት ሆስፒታል ሪፈር የተላኩ መኖራቸው ታውቋል። ይህን ጥቃት የፈጸሙት ጸረ አማራ የሆኑ የአዲስ አበባ የፖሊስ አባላት መሆናቸውን የገለጹት ምንጮች እንደሚሉት ደግሞ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ 2 የመከላከያ ሰራዊት እና 2 የፖሊስ አባላትን ጨምሮ 14 የሚሆኑ የማህበረ ስላሴ አባላትን ለ2 ቀናት አፍነው ከወሰዱ በኋላ በገንዘብ ዋስትና የፈቷቸው መሆኑ ተገልጧል። በዩኔስኮ ደረጃ የተመዘገበውን የጥምቀት በዓልን ለማድመቅ ብዙ የሰሩ እንዳሉ ሁሉ የተዛባ እይታ ያላቸው በዓሉን ለማደብዘዝ ስለመንቀሳቀሳቸው መረጃዎች ያመለክታሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply