“መንግስት በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በአስቸኳይ እንዲያስቆም፣በአጥፊዎች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ፣ መላው አማራ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንም በህወሀ…

“መንግስት በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በአስቸኳይ እንዲያስቆም፣በአጥፊዎች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ፣ መላው አማራ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንም በህወሀ…

“መንግስት በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በአስቸኳይ እንዲያስቆም፣በአጥፊዎች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ፣ መላው አማራ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንም በህወሀት ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በአንድነት እንዲደግፉ እንጠይቃለን!” የአማራ ማህበርና የአብን ድጋፍ ማህበር በጀርመን! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ህዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፀመው ሶቆቃና ፍጅት በአስከፊ ሁኔታ እንደቀጠለ መሆኑን የገለፁት የአማራ ማህበር እና የአብን ድጋፍ ማህበር በጀርመን ናቸው። ዛሬ ህዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም በጋራ ባወጡት መግለጫ በህዝባችን ላይ በኦነግ ሸኔ፣በቄሮ የጥፋት ሀይላትና በትህነግ ጥምር የሽብር ተግባር አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈፀመበት ነው ብለዋል። ለመላው አማራና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የአብሮነት ጥሪ ያቀረቡት ማህበራቱ አማራ ሰብአዊና የዜግነት መብቱ ተገፎ በመንግስት መዋቅር ጭምር በሚደገፈው የዘር ጥላቻና የማፅዳት ግፍ ሰለባ ሆኗል ብለዋል። አማራው ስለኢትዮጵያ ሰላምና የህዝብ ደህንነት ሲባል በትግስት ሲከፍል የኖረውና እየከፈለ ያለው ገደብ የለሽ መስዋዕትነት አንድም እንደ ሞኝነት ሁለትም እንደ ፍርሀት እየተቆጠረ በማንነቱና በሀይማኖቱ እንዲበደል መደረጉ በእጅጉ ያሳስበናል ነው ያሉት በላኩት መግለጫ። መንግስት የችግሩን አሳሰቢነት ተረድቶ በአጥፊዎች ላይ ተገቢ እርምጃ በመውሰድ ፋንታ ጥፋቱን ሲያድበሰብስ መቆየቱን ሀላፊነት የጎደለው ተግባር ነው ያሉት የአማራ ማህበር እና የአብን ድጋፍ ማህበር በጀርመን አካሄዱን አጥብቀን እንቃወማለን ብለዋል። አማራ ላለፉት 47 ዓመታት በትህነግ የተፈፀመበት እልቂት አልበቃ ብሎት ዛሬም በተረኛ ዘውጌ ፅንፈኛ መንጋ/ብሄርተኞች በሀሰት ትርክት ምክንያት እንደ ታሪካዊ ጠላት ተቆጥሮ የዘር ፍጅት በይፋ የታወጀበት መሆኑን የዶ/ር አብይ መንግስት በይፋ አምኖ እንዲቀበል ብሎም ሀላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል። ፀረ አማራ ሀይላት መከላከያ ሰራዊትን ከጀርባ በመውጋት በፈፀሙት ጭፍጨፋ ማዘናቸውን የገለፁት ማህበራቱ ድርጊቱን እኩይ ተግባር በመሆኑ ሁሉም ሊያወግዘው ይገባል ነው ያሉት። በመሆኑም መንግስት በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በአስቸኳይ እንዲያስቆም፣በአጥፊዎች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ፣ መላው አማራ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በህወሀት ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በአንድነት እንዲደግፉ ሲሉ የአማራ ማህበር እና የአብን የድጋፍ ማህበር በጀርመን በጋራ ጥሪ አቅርበዋል። በመጨረሻም የአማራ ማህበር እና የአብን የድጋፍ ማህበር በጀርመን ባለ10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል። ይኸውም:_ 1)በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በአስቸኳይ እንዲያስቆም፣በአጥፊዎች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ፣ 2)የአማራ ህዝብ እየደረሰበት ላለው የጅምላ ጭፍጨፋ በሰላማዊ መንገድ ቁጣውን እንዳይገልፅ መከልከሉንን አጥብቀን በመቃወም እንዳይደገም እንጠይቃለን፤ 3)የአማራ ህዝባዊ ሰራዊት ከመከላከያ ጋር በደጀንነት መሰለፉን የምንደግፈው ሲሆን ታሪካዊ እርስቱን ከማስከበርና ህዝቡን ከአደጋ ከመከካከል ባለፈ ከአሁን ቀደም እንደተደረገው አማራን ቀጥተኛና ግንባር ቀደም ተሰላፊ በማድረግ፣የጥቃቱም ሰለባ በማድረግ ታሪካዊ ስህተት እንዳይሰራ፣ 4)አማራ ታሪካዊ እና ባህላዊ አንድነቱን ጠብቆ የተቃጣበትን ጥቃት በራስ አድን ህጋዊ ንቅናቄ ለመከላከል ራሱን ከምንጊዜም በላቀ ያዘጋጅ፣ 5)በኦሮሚያና በሌሎች ክልሎች ያሉ የፀጥታ አካላት ከጎሳና ከፖለቲካ አድሎ ወጥተው የተጣለባቸውን ሀገራዊና መንግስታዊ ሀላፊነት ይወጡ፣ 6)በሀሰት ትርክት እና ፕሮፖጋንዳ ነፍጠኛና ሰፋሪ የሚለው የፀረ አማራ ሀይላት የቅስቀሳ ኮድ በህግ አግባብ ትክክለኛ ትርጓሜና እርምት እንዲሰጥበት እንጠይቃለን። 7)በፅንፈኛ ፀረ አማራ ሀይላት በአማራ ላይ ለደረሰው ኢሰብአዊ ጭፍጨፋና ጥቃት ፍትህ ለህዝባችን እያልን ለተጎጅዎች ተመጣጣኝ ካሳ እንዲከፈል እንጠይቃለን። 8)የጥፋት ሁሉ ምንጭ የሆነው ህገ መንግስት እንዲከለስ እንጠይቃለን። 9)አዲስ አበባ የሁሉም መዲና በመሆኗ በአንድ ጎሳ ለመጠቅለልና ለመዋጥ የሚደረገውን አካሄድ የማን አለብኝነት ተግባር በመሆኑ እናወግዛለን፤ በተያያዘ የባልደራስ እና የኢዴፓ አመራሮች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን። 10)ሁሉም የአማራ ሀይላትና አደረጃጀቶች ከምንጊዜውም በላይ በአንድ ላይ እንድትቆሙ ስንል ጥሪ እናቀርባለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply