You are currently viewing “መንግስት በአድዋ ድል በዓል በተፈጠረው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ኃላፊነት ሊወስድ ይገባል!” ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ገለጸ፤ ህዝቡን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅም ጥሪ…

“መንግስት በአድዋ ድል በዓል በተፈጠረው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ኃላፊነት ሊወስድ ይገባል!” ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ገለጸ፤ ህዝቡን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅም ጥሪ…

“መንግስት በአድዋ ድል በዓል በተፈጠረው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ኃላፊነት ሊወስድ ይገባል!” ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ገለጸ፤ ህዝቡን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅም ጥሪ አድርጓል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 27 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ኢሰመጉ በወቅታዊ ጉዳይ በሰጠው አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ በየካቲት 23/20215 ዓ.ም በተከበረው የአድዋ ድል በዓል ወቅት የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ከህብረተሰቡ የሚደርሱ ጥቆማዎችን እና መረጃዎችን መነሻ በማድረግና ባለሞያዎችን በመመደብ ሁኔታዎችን ሲከታተል ቆይቷል፡፡ የአድዋ በዓል ለ127ኛ ጊዜ ለማክበር የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንደወትሮው ለበዓሉ የሚዉሉ የዳግማዊ አፄ ሚኒሊክን እና የእቴጌ ጣይቱን ምስል የያዙ ካኒቴሪያዎችን ለማሳተም ከበዓሉ አንድ ሳምንት በፊት ጀምሮ በሽሮ ሜዳ አካባበቢ የአካባቢ ወጣቶችና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበር አውስቷል። የመንግስት ፀጥታ ኃይሎችም የካኒቴሪያዎቹ ህትመት እንዳይታተም በመከልከል ሱቆችንና ማተሚያ ቤቶችን በማሸግ የፀጥታ ኃይሎች ከህግ አግባብ ውጭ የሆነ ስራ ሲያከናውኑ እንደነበር ኢሰመጉ ካሰባሰበው መረጃ ለመረዳት መቻሉን ገልጧል፡፡ በበዓሉ ዋዜማ ዜጎች በዓሉን ለማክበር ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት አንዳንድ የፀጥታ አስከባሪዎች ወከባ፤ዛቻና አንዳንድ ተገቢ ያልሆኑ እርምጃዎችን ሲወስዱ እንደነበር ለመረዳት መቻሉን ጠቁሟል፡፡ በየካቲት 23 ቀን 2015 ዓ.ም ሕዝቡ 127ኛ የአድዋ ድል በዓልን በሚኒልክ አደባባይ ለማክበር በአካባቢው ለመታደም የሚመጡትን የሰንደቅ ዓላማ ምስል፣ የዳግማዊ አፄ ሚኒሊክንና የእቴጌ ጣይቱን ምስል ያለበትን ልብስ ለብሰው ወደ አደባባዩ እንዳይገቡ በመከልከል ዜጎች መብታቸውን እንዳይጠቀሙ ታግደዋል ብሏል ኢሰመጉ በመግለጫው፡፡ ይህም ሳይበቃ የፀጥታ ኃይሎች ህገወጥ የኃይል እርምጃ በመውሰድ የጪስ ቦምብ እና ፕላስቲክ ጥይት በመተኮስና ሕዝቡን በዱላ ጭምር በመደብደብ በዓሉን ለማክበር በታደሙ እንዲሁም በጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ታቦት ለማንገስ የወጡ ዜጎች ላይ የሕይወትና የአካል ጉዳት አድርሰዋል ሲልም አክሏል፡፡ በርካታ ዜጎችም ከዋዜማው ጀምሮ እንዲታሰሩ መደረጉን በሪፖርቱ ካታተው ኢሰመጉ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን እና በርካታ ሰዎችም ጉዳት እንደደረሰባቸው ማረጋገጡን ገልጧል፡፡ በመጨረሻም የሚከተሉትን ጥሪዎች አቅርቧል:_ 1) መንግስት በየጊዜው የአድዋ ድል በዓል ሲከበር እየተፈጠረ ያለውን ውዝግብና ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመፍታት ተገቢነት ያለውና ማህበረሰቡን ያማከለ ጀግኖች አባቶቻችን ኢትዮጵያ ሀገራችንን ለማቆየት የከፈሉትን ዋጋ ለትውልድ ለማስተላለፍ የሚጠቅም እርምጃ እንዲወስድ፤ 2) በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ የጪስ ቦምብ ምክንያት በንጹሃን ዜጎች ላይ ለደረሰው ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መንግስት ሕዝቡን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤ 3) በቅርቡ በተደጋጋሚነት እየተከሰተ ያለው የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚወስዱት ከመጠን ያለፈ የኃይል እርምጃና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንዲቆም መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርግ፤ 4) በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የሕይወትና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች መንግስት ተገቢውን ካሳ እንዲከፍል፤ 5) ከሕግ አግባብ ውጭ የታሰሩ ዜጎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ፤ 6) መንግስትና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በአዲስ አበባ ከተማም ሆነ በሀገሪቷ ዘላቂ ሰላም እንዲቀጥልና ሕዝቡ የተረጋጋ ሕይወት እንዲመራ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ጥሪውን አቅርቧል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply