You are currently viewing መንግስት በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በአማራዎች እና በሌሎችም ጭምር በአገር አፍራሽ ኃይሎች እየተፈጸሙ ያሉ ሁለንተናዊ ጥቃቶችን እንዲያስቆም ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

መንግስት በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በአማራዎች እና በሌሎችም ጭምር በአገር አፍራሽ ኃይሎች እየተፈጸሙ ያሉ ሁለንተናዊ ጥቃቶችን እንዲያስቆም ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

መንግስት በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በአማራዎች እና በሌሎችም ጭምር በአገር አፍራሽ ኃይሎች እየተፈጸሙ ያሉ ሁለንተናዊ ጥቃቶችን እንዲያስቆም ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 28 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በንጹሃን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እንደሚያሳስባቸው በመግለጽ መንግስት በተለይም በአማራዎችና በሌሎችም ጭምር የተከፈተውን ሁለንተናዊ ጥቃት እንዲያስቆም የጠየቁት ከአሚማ ጋር ቆይታ ያደረጉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት_መኢአድ እና የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ_ኢህአፓ አመራሮች ናቸው። በተለይም በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች የየክልሎችም ሆኑ የፌደራል መንግስት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ባለመወጣታቸው ምክንያት በአማራዎች ላይ ማንነት ተኮር የጅምላ ግድያ፣ እገታ፣መፈናቀልና ዝርፊያው ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል። ይህም ፓርቲያቸውን በእጅጉ እንደሚያሳስበው የገለጹት የመኢአድ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉጌታ አበበ እና የኢህአፓ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሀይማኖት ናቸው። አቶ ሙሉጌታ እንደአብነት ከሰሞኑ የእሳቸው የትውልድ አካባቢ በሆነው ጓህ ጽዮን አማራዎች በማንነታቸው ብቻ መጠቃታቸውን አውስተዋል። ይኽውም ሁለት አማራዎች በግፍ ተገድለው፤ ከ500 በላይ የአማራዎች መኖሪያ ቤት ተለይቶ በእሳት እንዲወድም የመደረጉን አሳዛኝ ሁኔታ አብራርተዋል። በርካታ የኦሮሚያ የመስተዳድር አካላት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድኑን ጥፋት እየተመለከቱ ንጹሃንን ለመታደግ ከመስራት ይልቅ በዝምታ መተባበራቸው ከምንም በላይ እንደ መኢአድም ሆነ እንደ ግል አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን አስምረውበታል። በተመሳሳይ መጋቢ ብሉይ አብርሃም በበኩላቸው ፓርቲያቸው ኢህአፓ በተለያዩ አካባቢዎች አሸባሪ አካላት በንጹሃን ወገኖች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት እንደሚያሳስበው ገልጸው መንግስት የሁሉንም ዜጎች በእኩልነት ደህንነታቸውን የማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል። አማራውን መምታት ማለት ኢትዮጵያን መምታት፣ ማዳከምና ማፍረስ ነው በሚል እሳቤ የተነሱ አፍራሽ ኃይሎች በአማራ ህዝብ ላይ ማንነት ተኮር ጥቃታቸውን እንደቀጠሉበት መሆኑንም ተናግረዋል። መንግስት መዋቅሩን መፈተሽ፣ ማጽዳት እና ማስተካከል አለመቻሉ አንደኛው ችግሩ ተደርጎ ተጠቅሷል። በሰሜን በኩል ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘም መንግስት ከቻለ ጦርነቱን በአጭር ጊዜ እና ውጤት ሊያመጣ በሚችል አግባብ ሊመራው እንደሚገባ ካልሆነለት ደግሞ ለኢትዮጵያ ህዝብ ቢሰጠው ሀገር ወዳዶች በአጭር ጊዜ ውስጥ በመከወን በስኬት እንደሚያጠናቅቁት ጠቁመዋል። ፖለቲከኞቹ እንዳሉት የየፓርቲዎቻቸው በየደረጃው ያሉ አባላትና አመራሮች በግንባር መሰለፍን ጨምሮ በተለያዩ መልኩ ዘመቻውን እያገዙ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply