መንግስት በደቡብ ክልል መዋቅሩን በመፈተሽ አዲስ ሪፎርም በመስራት ለሚፈጠሩ ግጭቶች አስቸኳይ እልባት መስጠት አለበት ሲሉ የሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን የመኢአድ ሰብሳቢ አቶ ገልገሎ ኮይታ ገለ…

መንግስት በደቡብ ክልል መዋቅሩን በመፈተሽ አዲስ ሪፎርም በመስራት ለሚፈጠሩ ግጭቶች አስቸኳይ እልባት መስጠት አለበት ሲሉ የሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን የመኢአድ ሰብሳቢ አቶ ገልገሎ ኮይታ ገለ…

መንግስት በደቡብ ክልል መዋቅሩን በመፈተሽ አዲስ ሪፎርም በመስራት ለሚፈጠሩ ግጭቶች አስቸኳይ እልባት መስጠት አለበት ሲሉ የሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን የመኢአድ ሰብሳቢ አቶ ገልገሎ ኮይታ ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ካለፈው 1997 ዓ.ም ጀምሮ በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ አባል ብሎም አመራር በመሆን እየታገሉ የሚገኙትን አቶ ገልገሎ ኮይታን አነጋግረናል። በደቡብ ክልል የሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን የመኢአድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ገልገሎ ኮይታ በ2002 ዓ.ም ውድ ባለቤታቸውን ከታጣቂዎች በተተኮሰ 22 ጥይት ተገድለውባቸዋል፤ ሁለት ልጆቻቸውም በጥይት ቆስለው አካል ጉዳተኛ ሆነዋል። የመኢአድ አመራር በመሆን በማገልገላቸው ብቻ ይህ ሁሉ ፈተና ቢገጥማቸውም አቶነገልገሎ ኮይታ ዛሬም በደቡብ ኢትዮጵያ በሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን የመኢአድ ሰብሳቢ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ። ከደቡብ ክልል ወደ አዲስ አበባ በመጡበት ወቅት ከጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሰገን፣አማሮ፣አሌ፣ኮንሶና ደራሼ አካባቢ ስለተፈፀመው ጭፍጨፋና መፈናቀል መረጃ እንዲሰጡን ጠይቀናል። አቶ ገልገሎ እንደገለፁት ጥቃቱ የተፈፀመውና እየተፈፀመ ያለው የመዋቅር ጥያቄን ለማዳፈን በሚፈልጉ በመንግስት መዋቅር ባሉ አመራሮች፣በልዩ ሀይሎችና በታጣቂዎች ነው ብለዋል። በዚህም በተለይ በአማሮ አካባቢ በአማራዎች ላይ የተፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀልና መፈናቀልን አስከፊነትን ጠቅሰው ነገሩ በፌደራል መንግስት ጣልቃ ገብነት መፍትሄ ሊበጅለት ይገባል ብለዋል። መኢአድ የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት ብሎም ለሚመለከታቸው አካላት እየጠየቀ መሆኑን ያስታወቁት አቶ ገልገሎ ለችግሩ መፍትሄውም መዋቅሩን በመፈተሽ አዲስ ሪፎርም ማድረግ ብሎ ያምናል ብለዋል። ከአቶ ገልገሎ ኮይታ ጋር የተደረገውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply