You are currently viewing መንግስት በፍርድ ሂደት የነበሩ ሰዎችን ክስ በማቋረጥ ከእስር እንዲለቀቁ ማድረጉ ሕዝቡን ለከፍተኛ ግራ መጋባት ያጋለጠ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ በቂ ማብራሪያ እንዲሰጥ ሲል የሲቪል ማኅበረሰብ ድር…

መንግስት በፍርድ ሂደት የነበሩ ሰዎችን ክስ በማቋረጥ ከእስር እንዲለቀቁ ማድረጉ ሕዝቡን ለከፍተኛ ግራ መጋባት ያጋለጠ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ በቂ ማብራሪያ እንዲሰጥ ሲል የሲቪል ማኅበረሰብ ድር…

መንግስት በፍርድ ሂደት የነበሩ ሰዎችን ክስ በማቋረጥ ከእስር እንዲለቀቁ ማድረጉ ሕዝቡን ለከፍተኛ ግራ መጋባት ያጋለጠ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ በቂ ማብራሪያ እንዲሰጥ ሲል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት ለኢትዮጵያ አሳሰበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ውሳኔው በህዝቡ ዘንድ ግርታን ከመፍጠሩ ባሻገር የተለያዩ አገራትን አሰላለፍ ጭምር ሊቀይር የሚችል በመሆኑ መንግስት ተጨማሪ ማብራሪያዎችን መስጠት ቀዳሚ ስራው ሊሆን እንደሚገባ ነው ያሳወቀው፡፡ ውሳኔው አገርንና ህዝብን የሚያሳጣው አንዳች ነገር እንዳይኖርም መንግስት መጠንቀቅ ይኖርበታል ሲሉ ለአሐዱ የገለፁት የጥምረቱ ፕሬዝዳንት ጋሻው ሽባባው ናቸው፡፡ ፕሬዝዳንቱ አገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የአሁኑ ውሳኔ ለሌላ ችግር የሚዳርግ እንዳይሆን ጥንቃቄዎች መደረግ እንደሚገባቸውም አመላክተዋል፡፡ መንግስት በቂ መረጃዎችን ለህዝቡ እንዲደርስ በማድረግ ሊደርሱ የሚችሉ ስጋቶችን ከወዲሁ መቀነስ ይኖርበታል ሲሉም አክለዋል፡፡ መንግስትም ይሁን ሌሎች ወገኖች በየትኛውም አኳኋን የህዝብን ቁጣ ከሚቀሰቅሱ ማናቸውም ደርጊቶች መቆጠብ እንደሚገባቸውም ስለማሳሰቡ አሀዱ ሬዲዮ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply