
መንግስት በፖለቲካ አመለካከታቸውና በመንግስት አሰራሮች ላይ በሚያቀርቡት የፖለቲካ ትቺት ምክንያት፤ ወንድማችንን ዘሪሁን ገሰሰን ጨምሮ፥ በተለያዩ አካባቢዎች ያሰራቸውን የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈታ ተጠየቀ። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 4/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ መንግስት በፖለቲካ አመለካከታቸውና በመንግስት አሰራሮች ላይ በሚያቀርቡት የፖለቲካ ትቺት ምክንያት፤ ወንድማችንን ዘሪሁን ገሰሰን ጨምሮ፥ በተለያዩ አካባቢዎች ያሰራቸውን የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈታ የጠየቀው የሕዝብ እንደራሴ አቶ ክርሰቲያን ታደለ ነው። ዘሪሁን ገሰሰን ጨምሮ፥ በተለያዩ አካባቢዎች ያሰራቸውን የፖለቲካ እስረኞች ስለመኖራቸው በመግለጽ በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱ ጥሪ አድርጓል። ፓርቲ የመሰረትነው መንግስትን መቼና እንዴት መተቼት እንዳለብን ከራሱ ከመንግስት አቅጣጫ እየተቀመጠልን ለመንቀሳቀስ አይደለምና፥ በተለይም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በትንሹ የራሱን አባላት ደኅንነት የማስጠበቅ ግዴታውን በወጉ እንዲወጣም በአንክሮ ጠይቋል።
Source: Link to the Post