“መንግስት ችግሮችን ቀድሞ የመከላከል ፍላጎት አጥቷል” ሲሉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሊቀመንበር አቶ ማሙሸት አማረ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥቅምት 9 ቀን…

“መንግስት ችግሮችን ቀድሞ የመከላከል ፍላጎት አጥቷል” ሲሉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሊቀመንበር አቶ ማሙሸት አማረ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 9 ቀን…

“መንግስት ችግሮችን ቀድሞ የመከላከል ፍላጎት አጥቷል” ሲሉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሊቀመንበር አቶ ማሙሸት አማረ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ “መንግስት ችግሮችን ቀድሞ የመከላከል ፍላጎት አጥቷል” ሲሉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መኢአድ/ ሊቀመንበር አቶ ማሙሸት አማረ ተናግረዋል፡፡ አቶ ማሙሸት ከአሻራ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት እየተከሰቱ ያሉ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ችግሮችን ቀድሞ ከመከላከል አንፃር መንግስት ፍላጎት አጥቷል ብለዋል፡፡ በሀገር ላይ ሊከሰቱ ይችላሉ ተብለው በስጋት የተለዩ ችግሮችን መንግስት ዝግጁነት ወስዶ እና ተንብዮ መቀመጥ ይኖርበታል ብለዋል፡፡ የአርሶ አደሩን ልፋት ከንቱ እያስቀረ ያለውን የበረሀ አንበጣ መንጋም መንግስት ቀድሞ ዝግጁነት ቢኖረው ኖሮ ጥፋት ሳያስከትል መከላከል ይቻል እንደነበር አንስተዋል፡፡ ነገር ግን ከአንድ አመት በፊት ጀምሮ የአንበጣ መንጋ እንደሚከሰት ትንበያዎች እየወጡ መንግስት በቸልታ በመመልከቱ ዛሬ ላይ ከፍተኛ ውድመት ማስከተሉን ገልፀዋል፡፡ የሀገሪቱ የጀርባ አጥንት የሆነው የግብርናው ኢኮኖሚ ከተጎዳ ሀገሪቱ ወደ ከፍተኛ ቀውስ ልትገባ እንደምትችል ያስጠነቀቁት አቶ ማሙሸት የኬሚካል ርጭት የሚያካሂዱ አውሮፕላኖች ግዥም ሆነ ኪራይ በአፋጣኝ ሊከናወን ይገባል ብለዋል፡፡ የአንበጣ መንጋው ባስከተለው ጉዳት ሰብላቸው ለወደመባቸው አርሶ አደሮችም አፋጣኝ ድጋፍ እንዲደረግላቸው አሳስበዋል፡፡ ህወሀት መራሹ ኢህአዴግ ሀገሪቱን ሲያስተዳደር ከነበረበት ጊዜ በባሰ ሁኔታ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በአማራዎች ላይ ጥቃቶች እየተፈፀሙ መሆኑን የገለፁት አቶ ማሙሸት ይህም ሊሆን የቻለው ከ1960ዎቹ ጀምሮ በአማራ ላይ የተዘራው የጥላቻ ትርክት ወደ ተግባር እየተለወጠ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ በመተከል ዞንና አካባቢው በአማራዎች ላይ ለሚፈፀመው ጥቃትም አካባቢውን በሀላፊነት ባለማስተዳደር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ አመራሮች ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡ አሻራ ሚዲያ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply