መንግስት እና ያገባናል የሚሉ አካላት የሚልኩልን እርዳታ በሚዲያእንደምንሰማውና እንደምናዬው በተግባር እየደረሰን አይደለም ሲሉ በቡለን ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች ቅሬታ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማ…

መንግስት እና ያገባናል የሚሉ አካላት የሚልኩልን እርዳታ በሚዲያእንደምንሰማውና እንደምናዬው በተግባር እየደረሰን አይደለም ሲሉ በቡለን ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች ቅሬታ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማ…

መንግስት እና ያገባናል የሚሉ አካላት የሚልኩልን እርዳታ በሚዲያእንደምንሰማውና እንደምናዬው በተግባር እየደረሰን አይደለም ሲሉ በቡለን ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች ቅሬታ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 29 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ብቻ ከ51 ሽህ በላይ ተፈናቃዮች እንዳሉ የገለፁት የአማራ ሚዲያ ማዕከል ምንጮች ከእርዳታ እና ከህክምና ጋር በተያያዘ ያሉ ችግሮች እየፈተኗቸው መሆኑን ተናግረዋል። መንግስት እና ያገባናል የሚሉ አካላት የሚልኩልን እርዳታ በሚዲያ እንደምንሰማውና እንደምናዬው በተግባር እየደረሰን አይደለም ሲሉ ነው ቅሬታቸውን ያሰሙት። ይባስ ብሎ ለተፈናቃዮች ተብሎ የሚላክ እርዳታ መንግስት በተፈናቃይነት ለማያውቀው አካል ተላልፎ እየተሰጠብን ነው ሲሉ ወቅሰዋል። እንደአብነት ሲጠቅሱም ታህሳስ 28 ቀን 2013 ዓ.ም አንድ አይሱዙ ሙሉ ቀለብ ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ ከቡለን ወረዳ በመጫን ወደ ተፈናቃዮች ወደሌሉበት ማጣ ቀበሌ ይዞ ሲወጣ የነበረ ሀብቴ አበበ የተባለ የጭላንቆ የቀበሌ ም/አስተዳዳሪ በተፈናቃዮች ተቃውሞ በቡለን ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩንና ጭነቱም እንዲቀር መደረጉን ጠቁመዋል። የጭላንቆ ቀበሌ ም/አስተዳዳሪ አቶ ሀብቴ አበበ ከቡለን ከተማ ጭኖ ወደ ማጣ ቀበሌ ይዞ ሲሄድ ለየትኛው ተፈናቃይ ልትሰጠው ነው በማለት ነው ተቃውሞ የተነሳበት ተብሏል። ሌላ አንድ አይሱዙ ቀለብ ግን ከአሁን ቀደም ወደ ማጣ ቀበሌ ተጭኖ ያለፈ ስለመሆኑም ነዋሪዎች ተናግረዋል። ተፈናቃዮች አያይዘውም ወላዶች፣ህፃናትና አቅመ ደካሞች ለሚያጋጥማቸው ህመም ህክምና በወቅቱ እያገኙ አለመሆኑን ገልፀዋል። መንግስት አሁንም ሰብአዊ ድጋፍ በማደረግ ረገድ እየደረሰልን አይደለም ያሉት ምንጮች ጨፍጫፊዎቹ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተፈናቃዮችን ደግመው ሊያጠቁ እንደሚችሉ እየዛቱ መሆናቸውንም አስታውቀዋል። ዛሬ ታህሳስ 29 ቀን 2013 ዓ.ም ከግልገል በለስ ከተማ መተከል ዞን የመጣን ነን ያሉ አመራሮች ከእርዳታ ጋር ተያይዞ ያለው ችግር እንዶፈታ እንሰራለን ስለማለታቸው የገለፁት ምንጮች የቡለን ወረዳ ወጣቶችና ነዋሪዎች ለበዓል መዋያ እንዳገዟቸው በማውሳት አመስግነዋል። አሚማ የምግብ ዋስትና እና ሌሎች የሚመለከታቸውን የመንግስት አካላት የስልክ አድራሻ እንዳገኘ ምላሻቸውን ለማካተት ዝግጁ መሆኑን ያሳውቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply