መንግስት እየወሰደ ባለው የህልውና ዘመቻ እና ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የኦሮሞ ዳያስፖራ አባላት እየተወያዩ ነው

መንግስት እየወሰደ ባለው የህልውና ዘመቻ እና ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የኦሮሞ ዳያስፖራ አባላት እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት እየወሰደ ባለው የህልውና ዘመቻ እና ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የኦሮሞ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ውይይት እያካሄዱ ነው።

የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያዘጋጀው ውይይት የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ታዬ ደንደአ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ ሌንጮ ባቲ በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

በውይይቱ ላይ አትሌቶች እና አርቲስቶችን ጨምሮ በዳያስፖራው ማህበረሰብ ዘንድ ተሰሚነት ያላቸው የኦሮሞ ዳያስፖራዎች ተሳታፊዎች ናቸው።

የኦሮሞ ዳያስፖራ የሀገር ውስጥ ሁለንተናዊ ተሳትፎ እንዲሁም ወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳይ የውይይቱ ዋነኛ አጀንዳዎች ናቸው።

በመድረኩ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መነሻ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት እየተካሄደበት ይገኛል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

The post መንግስት እየወሰደ ባለው የህልውና ዘመቻ እና ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የኦሮሞ ዳያስፖራ አባላት እየተወያዩ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply