መንግስት ከሱዳን ጋር በመነጋገር በማይካድራ አማራ ላይ የጅምላ ፍጅት የፈፀሙ የሕወሓት ነፍሰ ገዳዮችን በአስቸኳይ ይዞ በሕግ ተጠያቂ እንዲያደርግ ሲሉ የማይካድራ ነዋሪዎች ጠየቁ። አማራ ሚዲያ…

መንግስት ከሱዳን ጋር በመነጋገር በማይካድራ አማራ ላይ የጅምላ ፍጅት የፈፀሙ የሕወሓት ነፍሰ ገዳዮችን በአስቸኳይ ይዞ በሕግ ተጠያቂ እንዲያደርግ ሲሉ የማይካድራ ነዋሪዎች ጠየቁ። አማራ ሚዲያ…

መንግስት ከሱዳን ጋር በመነጋገር በማይካድራ አማራ ላይ የጅምላ ፍጅት የፈፀሙ የሕወሓት ነፍሰ ገዳዮችን በአስቸኳይ ይዞ በሕግ ተጠያቂ እንዲያደርግ ሲሉ የማይካድራ ነዋሪዎች ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሽብር ተግባር የተሰማራውና ዘረኛ የሆነው የሕወሓት ነፍሰ ገዳይ ስብስብ ባለፉት በርካታ ዓመታት የማንነት ጥያቄ አነሳችሁ በሚል በወልቃይት፣ጠገዴና ራያ አማራ ላይ ሲፈፅመው የነበረው ግድያ፣እስር፣አፈና እና የማፈናቀል ወንጀል ለመናገርም የሚቸግር መሆኑን ነዋሪዎች አውስተዋል። በማይካድራ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ልዕልት ቸኮል ሕወሓት ሳምሪ የተባለ የነፍሰ ገዳዮችን ስብስብ፣እንዲሁም ልዩ ሀይልና ሚሊሻዎችን በማሰማራት በሆቴልሽ የአማርኛ ሙዚቃ ከፍተሻል በሚል ሰበብ ቤታቸው በድንጋይ እንዲደበደብ ከማድረግ በተጨማሪም ለተደጋጋሚ እስር ሲዳረጉ ከነበሩት አማራዎች መካከል አንዷ ናቸው። ወ/ሮ ልዕልት በማይካድራ በተፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል በእጅጉ ማዘናቸውን ገልፀው አሁን ላይ በየቦታው የወደቀውን አስከሬን በማፈላለግ በክብር እየቀበሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። በጨካኞች በግፍ ከተገደሉት መካከልም አማራ ነኝ ብለሀል በሚል በተደጋጋሚ ሲያስሩትና ሲፈቱት የነበረውን አቶ አማረ ጥሩነህን ጨምሮ ፀሀዬ፣ጀማልና አወቀን የጠቀሱት ነዋሪዋ ብዙ አድራሻቸው ያልታወቁ አማሮች አሉ ሲሉም ተደምጠዋል። ወልቃይት፣ጠገዴ፣ራያ አማራ ስለመሆኑ የተናገሩት ወ/ሮ ልዕልት ዳግም ወደ ትግራይ መስተዳድር መካለል የሚለው ወጉ እንኳ መታሰብ እንደሌለበት ነው የገለፁት። በማይካድራና በሁመራ ጭፍጨፋ የፈፀሙት ሕወሓት ያሰማራቸው ነፍሰ ገዳዮች በስደተኝነት ስም ወደ ሱዳን ከገቡ በኋላም አላረፉም ሲሉም አክለዋል። ዛሬም ሱዳን በሚገኙ አማራዎች ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ ልዕልት እንደአብነትም በሱዳን በሚኖር ልጃቸው ላይ ጥቃት ሊፈፅሙ መሆኑን በደረሳቸው መረጃ መሰረት ልጃቸውን ወደ ጎንደር ማስመጣታቸውን አውስተዋል። የሕወሓት ካድሪና ባለሀብት እንደሆነ የተነገረለት አቶ መንግስቱ ሀድጎም የራሱን ንብረት ወደ ሱዳን ካጓጓዘ በኋላ ከ3 ቀናት በፊት የወልቃይት ጠገዴ ሰሊጥን ዘርፎ ስለመውሰዱ ተገልጧል። ማይካድራ ላይ በሕወሓት ሚሊሻነትና ካድሪነት ስታገለግል የነበረችው ግደይ ባርነሞና ወደ ሱዳን ከእነ ጦር መሳሪያ እንደገባችና በገዳሪፍ አቸባ በተባለ የስደተኛ ካምፕ ሆና ለቀን ስራ በሄዱ አማራዎች ላይ ስለላ በመስራት እያሳደደችና እያስፈራራች መሆኑ ተነግሯል። በተጨማሪም በማይካድራ አስከፊ ግድያ የፈፀሙት እነ የማነ ሸሪፎ፣ አቶ ሀለፎም፣መ/ር ተሻገርና ሌሎችም ከስደት ሆነው ያረፉ ባለመሆናቸው ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ተጠይቋል። ሳምሪዎች በሱዳን እየፈፀሙት ያለውን ማሳደድ ተከትሎም ትናንት ህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም ሁለት ትራክተር ሙሉ አማራዎች ከሱዳን ወደ ማይካድራ ተመልሰዋል ብለዋል። የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ጨምሮ የአማራ ልዩ ሀይሎች፣ሚሊሻዎች፣ፋኖዎችና የመከላከያ ሰራዊት ህዝቡን እያወያዩ፣ እያረጋጉትና ወደ መደበኛ ህይወቱ እንዲመለስ እያደረጉ እንደሚገኙ ነው ወ/ሮ ልዕልት የተናገሩት። ከወ/ሮ ልዕልት ቸኮል ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ የምናጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply