
መንግስት ከሸኔ ጋር ለመደራደር አስር ጊዜ ሙከራ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
የፌደራሉ መንግስት ከአሸበሪዉ “ኦነግ ሸኔ” ጋር ለመደራደር 10 ጊዜ ሙከራ አድርጎ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ አስታዉቀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሳላቸዉ ጥያቄ ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነዉ፡፡
ከሸኔ ጋር ለሚደረገዉ ድረድርም መንግስት ኮሚቴ አዋቅሮ ወደ ሥራ እንደገባ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ቀደም የተደረገዉ ድርድር ሙከራ ያልተሳካዉ የሸኔ ኃይል የተበታተነ በመሆኑ ነዉ ብለዋል፡፡
መንግስት ከሸኔ ጋር ያለዉን ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ፅኑ ፍላጎት እንዳለዉም ተነስቷል፡፡
በቅርቡ የኦሮሚያ ከልል ለሸኔ ያቀረበዉ የእንደራደር ጥያቄ የክልሉ ዉሳኔ ሳይሆን የፌደራሉ መንግስት ዉሳኔ እንደሆነም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በማብራሪያቸዉ አንስተዋል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን
Source: Link to the Post