You are currently viewing መንግስት ክስ የማቋረጥ ውሳኔዉን እንዲያስተካክል የአለም አቀፍ ዳያስፖራ ሕብረት ጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ጥር 3 ቀን 2014 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ የአለም አቀፍ ኢ…

መንግስት ክስ የማቋረጥ ውሳኔዉን እንዲያስተካክል የአለም አቀፍ ዳያስፖራ ሕብረት ጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 3 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአለም አቀፍ ኢ…

መንግስት ክስ የማቋረጥ ውሳኔዉን እንዲያስተካክል የአለም አቀፍ ዳያስፖራ ሕብረት ጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 3 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአለም አቀፍ ኢትዮጵያዊያን የተባበረ ዳያስፖራ ሕብረት ስብሃት ነጋና እንደሳቸው በህግ ስር የነበሩ የጦር ወንጀለኞችን በመፍታት የተወሰደው እርምጃ ትክክል ባለመሆኑ መንግስት ማስተካከያ እርምጃዎችን እንዲወስድ ጠይቋል። መንግስት የሰጠውን ክስ የማቋረጥ ውሳኔ በማስተዋል በአስቸኳይ እንዲያስተካክልና የሕዝብን ወሳኝነት፣ ክብርና ልዕልና ከግምት ያስገባ ሕዝባዊ አካሄድን እንዲያጠናክርና በጊዜያዊ አቋራጭ ውሳኔዎች ዘላቂውን የሕዝብ አመኔታና ብሎም ሰላም እንዳያናጋ ጥንቃቄ እንዲደረግ ጥሪ አስተላልፏል። ሕብረቱ በትላንትናዉ እለት ባወጣዉ መግለጫ ስብሐት ነጋና ግብረአበሮቹ ያላቸው ላለፉት 27 አመታት ኢትዮጲያን እንዳፈረሱና ንብረቷን እንደዘረፉ ህዝቡንም ለስደትና ለእንግልት እንደዳረጉት አለም በሙሉ የሚያውቀው ሐቅ ነው ብሎታል። በጥፋታቸው ተፀፅተው የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ሳይጠይቁና ትጥቃቸውን ሳይፈቱ ክስ ማቋረጥ የፍትህ ስርአቱን ታአማኒነት አደጋ ላይ ይጥላል ብሏል። የኢትዮጵያ መንግስት ወንጀለኞችን መፍታት የሰጠው ምክንያት በሐገሪቱ ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀን ቡድን እየመሩ በሰሜን እዝ ሰራዊት ላይ ክህደት በመፈፀም ሀገርን ካወደሙ ሕዝብ በጅምላ ካስገደሉና አልፈው ተርፈው የሐገርን ሉአላዊነት አደጋ ላይ ለመጣል ተራራ ስር መሽገው ሲዋጉና አመራር ሲሰጡ ለነበሩት ስብሐት ነጋና መሰሎቻቸው በቂ ምክንያት እንዳልሆነ ህብረቱ ጨምሮ ገልጧል ሲል ኢትዮ መረጃ ኒውስ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply