መንግስት የመጡልኝ የካሳ ጥያቄዎች መመለስ አልችልም አለ፡፡

እነዚህ የካሳ ጥያቄዎች የልማት ስራዎቼን እያስተጓጎሉብኝ ናቸውም ብሏል፡፡

መንግስት የተጠየቀውን እና የመጣውን የካሳ ጥያቄ ሁሉ የመክፈል አቅም የለውም ተብሏል፡፡
ይህንን ያለው የገንዘብ ሚኒስትር ነው፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እየገመገመ ይገኛል፡፡

በግምገማው ላይ የተገኙት የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ እንደተናገሩት መንግስት በሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች የካሳ ጥያቄ ዋነኛ ችግር ሆኖ ይገኛል ብለዋል፡፡

የፌደራል ፕሮጀክቶች በሚተገበሩበት ወቅት ሚመጣው የካሳ ጥያቄ እጅግ የተጋነነ እና ከመንግስት እቅም የሚፈትሽ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

የሚመጣው እና የሚጤቀው የካሳ ጥያቄ ከመንግስት አቅም ጋር የሚጣጣም አይደለም ብለዋል፡፡

በመሆነም መንግስት ተገምቶ የመጣ የካሳ ጥያቄ ሁሉ የመክፍል አቅም የለውም ብለዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply