መንግስት የሚመራውን ከተማ መልካም ስም ይገነባል እንጅ እንዴት ሰላማዊዋን ከተማ በሽብር ዜና ያናውጣል! ሰ.አሜሪካ:- ሰኔ 21/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የሀገ…

መንግስት የሚመራውን ከተማ መልካም ስም ይገነባል እንጅ እንዴት ሰላማዊዋን ከተማ በሽብር ዜና ያናውጣል! ሰ.አሜሪካ:- ሰኔ 21/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የሀገሪቱ ሁሉም ሚዲያወች እና የመንግስት አክቲቪስቶች ስለ ባህርዳር የሽብር ዜና እያወሩ መሆኑን ሰምቸ በሰው ወይም በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት እንዳለ ብየ ሰግቸ ነበር። ምንም ዓይነት ጉዳት አለመድረሱን አጣራሁ። ፋኖወችን ማሰር ከተፈለገ እኮ ቦንብ ማጮህ ሳያስፈልግ እንደሌላው አካባቢ ማሰር ይቻል ነበር። ለዚህ ተብሎ ውቢቷን የቱሪስት ከተማ መልካም ስም ማጥፋት ግን ከተማዋን ከሚያስተዳድር አካል የሚጠበቅ አይደለም። በሌላ በኩል ብዙ ሰው ፋኖ እንዴት ከተማ ሊገኝ ይችላል የሚል ጥያቄ ሲያነሳ አይቻለሁ። ከፊሉ የዚህ ጥያቄ ባለቤት የእለት ስንቅ ማቀበል የማይችል ተቺ ቢሆንም ጥያቄዉን መመለስ ግን ተገቢ ስለሆነ ያለኝን መረጃ ላካፍላችሁ። ባጣራሁት መሰረት የባህርዳር ፋኖዎች የአፈና ዘመቻው የተጀመረ አካባቢ ከከተማ ወጥተው ነበር። ሆኖም የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊው ኮ/ር አትንኩት እና የሰላም እና ደህንነት መምሪያ ኃላፊው አቶ አደራውን ጨምሮ ሌሎች የፀጥታ አመራሮች በሰው በኩል ካገኟቸው በኋላ “… መንግስት እናንተን ማሰር አይፈልግም፣ ከቻላችሁ እነ ዘመነን ከመንግስት ጋር የማግባባት ስራ እንዲሰራ አግዙን…” የሚሉ እና ሌሎችም ሃሳቦች አቅርበውላቸው እነሱም ማለት የሚገባቸዉን ተናግረው ለግማሽ ቀን ውይይት ካደረጉ በኋላ ነበር ከጫካ ወደ ከተማ የተመለሱት። ከከተማዋ አመራር ጋርም ቢሆን በአንፃራዊነት መልካም የሚባል ግንኙነት ነበራቸው። ለማንኛውም ከታፈኑት የሀገር ባለውለታወች ጎን እንቁም‼️ © ጠበቃ አስረስ ማረ ዳምጤ #በቃ! #እምቢ! #AmharaGenocide! ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply