መንግስት የሱዳን ጦር እያደረሰ ያለውን ግድያ፣ እገታ፣ዝርፊያና ማፈናቀልን በውል ተገንዝቦ ምላሽ እንዲሰጥ እየተጠየቀ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ጥር 2 ቀን 2013 ዓ.ም…

መንግስት የሱዳን ጦር እያደረሰ ያለውን ግድያ፣ እገታ፣ዝርፊያና ማፈናቀልን በውል ተገንዝቦ ምላሽ እንዲሰጥ እየተጠየቀ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 2 ቀን 2013 ዓ.ም…

መንግስት የሱዳን ጦር እያደረሰ ያለውን ግድያ፣ እገታ፣ዝርፊያና ማፈናቀልን በውል ተገንዝቦ ምላሽ እንዲሰጥ እየተጠየቀ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 2 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የሱዳን ጦር የሀገር ሉአላዊነት ከተዳፈረ ሰነበተ፤ በኢትዮጵያ በኩል ችግሩን በሰላማዊ መንገድ እንፍታው በሚል እያቀረበች ላለው ጥሪም ቀና ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በመተማ፣በቋራ፣በምዕራብ አርማጭሆና በማይካድራ የልማት ቀጠናዎች ከባድ መሳሪያ የታጠቀ ከፍተኛ ወራሪ ጦር በማሰማራት ጉዳት እያደረሰ ይገኛል። ይህ ተስፋፊ ጦር ብቻውን አለመሆኑና ይልቁንስ የከሃዲው የትሕነግ እና የግብጾች እጅ እንዳለበትም እየተነገረ ነው። በመተማ በኩል ቱመት መንዶካ ቀበሌ ለሱዳን መረጃ የሚያቀብሉ የናይጀሪያ ፈላታዎች ከአንድ ሳምንት በፊት 7 የቀን ሰራተኞችን አግተው አንዱን መግደላቸውንና ሌላኛውን ማቁሰላቸው፣ የ5ቱን ደብዛ ማጥፋታቸው ተገልጧል። የሱዳን ጦር እንደአብነትም ድንበር ጥሶ በመግባት በመተማ በኩል የእነ መልካሙንና ወ/ሮ ለምለምን፣ የእነ አደራጀውን፣ በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የእነ አሰማራው መኮንን፣ባሻ ጥጋቡ፣ጋሻው እንዳልክ፣ ሰለሞን በየነና የመሳሰሉትን ባለሀብቶች የእርሻ ካምፕ በመቆጣጠር መዝረፉና ማቃጠሉ ይታወቃል። ሀብት ንብረት ከመዝረፍና ከማቃጠሉ ባሻገርም ከእለተ ሰኞ ታህሳስ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ማክሰኞ እና ረቡዕ በማይካድራ ዙሪያ ሊጉዲ በተባለ አካባቢ የሱዳን ጦር በአርሶ አደሮች ላይ ከበባ ተኩስ ከፍቶ እንደነበር ምንጮች ተናግረዋል። በዚህም ወጣት ማማይ ደሴ የተባለ የታች አርማጭሆ ወረዳ ወጣት ማክሰኞ እለት ታህሳስ 27 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ከሱዳን በተተኮሰ ጥይት መገደሉ ተገልጧል። የወጣት ማማይ ስርዓተ ቀብርም ታህሳስ 28 ቀን 2013 ዓ.ም በታች አርማጭሆ ወረዳ ሳንጃ ስለመፈፀሙ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በወቅቱ በሊጉዲ አፈና የተደረገብን መሆኑን በመግለፅ ድረሱልን በማለት የጠየቅን ቢሆንም አልታዘዝንም በሚል ፈጥኖ የሚደርስ አካል አለማግኘታቸውም በክፍተት ተጠቅሷል። በመጨረሻም መንግስት የሱዳን ጦር ከትሕነግ የሽብር ቡድንና ከሌላም ጋር በመተባበር በድንበር አካባቢ ተደራራቢ ጉዳት እያደረሱ እንደሚገኙ በውል ተገንዝቦ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ነው እየተጠየቀ ያለው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply